
ባሕር ዳር፡ ሕዳር 14/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አርቲስት ቴድሮስ ተሾመ የህልውና ዘመቻውን መቀላቀሉን “የኔ ማለፍ ሀገሬን የሚያቆያት ከሆነ ለመሠዋት ዝግጁ ነኝ” በማለት አስታውቋል።
አርቲስት ቴድሮስ ተሾመ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባስተላለፈው መልእክት “ሀገራችን ከምን ጊዜውም በላይ ትፈልገናለች። አሁን ትግሉ ከኮምፒውተሩና ስልኩ አልፎ በአካል ሊሆን ግድ ብሏል።
መተኮስ እችላለሁ። የኔ ማለፍ ሀገሬን የሚያቆያት ከሆነ ለመሰዋትም ጭምር ዝግጁ ነኝ። ኢትዮጵያዊ ከሆንክ፣ ሙሉ የአካል ብቃት ካለህ፣ ይህ እድል እንዳያመልጥህ። ና! በጋራ ሀገር እናኑር። በዚህ ወቅት አንተ ሙሉ ብቃቱ እያለህ ለሀገርህ ዘብ ለመሆን ካመነታህ ነገ በልጆችህ ፊት ታሪክ ሲወቅስህ ትሸማቀቃለህ!! እህቴ መልእክቱ ላንቺም ጭምር ነው። ትግል ሜዳ እንገናኝ። ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!” ሲል ጥሪውን አስተላልፏል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ