“ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ግንባር አቅንተው እኔ ቤት የምቀመጥበት አንድም ምክንያት የለም” ብርጋዴር ጀነራል ካሳዬ ጨመዳ

325
ሕዳር 14/2014 (አሚኮ) “ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ግንባር አቅንተው እኔ ቤት የምቀመጥበት አንድም ምክንያት የለም፤ ያለኝን የውትድርና ጥበብ ተጠቅሜ ጠላትን ድል ለማድረግ ዝግጁ ነኝ ” ሲሉ ብርጋዴር ጀነራል ካሳዬ ጨመዳ ገለጹ፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ግንባር ማቅናት ግንባር ላይ እየተዋደቀ ለሚገኘው ሠራዊት ከፍተኛ መነሳሳትና የሞራል ሰንቅ ይሆነዋል ብለዋል፡፡
ጀነራሉ አክለውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ውሳኔ መወሰናቸው ኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ ውስጥ ጠላትን ድል ለማድረግ ያግዛታልም ብለዋል፡፡
ሠራዊቱ መሪው ጎን ሆኖ ሲዋጋ እንዴት ድል ማድረግ እንዳለበት ያውቅበታል ሲሉም ጠቁመዋል፡፡
“እኔም አንድ ልጄን ይዤ በማንኛውም ሰዓት መከላከያ በሚፈልገው ቦታ ለሀገሬ መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ ነኝ” ብለዋል፡፡
ግንባር በመሄድ ያለኝን ውትድርና ጥበብ ተጠቅሜ ጠላትን በመደምሰስ ኢትዮጵያን ለማዳን ተዘጋጅቻለው ሲሉም ተናግረዋል፡፡
መላው የኢትዮጵያ ሕዝብም የጠቅላይ ሚኒስትሩን አርዓያ በመከተል ወደ ግንባር ማቅናት ያለበት በመዝመት፤ ሌላው ደግሞ በመደገፍ ለሀገሩ አስፈላጊውን ሁሉ ማድረግ ይኖርበታልም ብለዋል፡፡
በተለይም የቀድሞ ሠራዊት አባላት ለዚህ ጥሪ ግንባር ቀደም በመሆን ትናንት ለሀገራቸው የከፈሉትን መስዋእትነት ዛሬም መድገም አለባቸው ሲሉ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
“ኢትዮጵያ” የሚለውን የነጻነት ስም የማስጠበቅ የታሪክ አደራ አለብን! ከእንግዲህ እኔ መከላከያን በግንባር ሆኜ ለመምራት ወደ ትግሉ ሜዳ እዘምታለሁ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) መግለጻቸው ይታሰወሳል፡፡
ተነሳ!!
መሪህን ተከተል!!
ሀገርህን አድን!!
ነፃነትህን አትስጥ !!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል በአዲስ አበባ እና በዙሪያው ለሽብር ተግባር ያሰማራቸው ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ።
Next article❝የሸዋ ተራራዎች የሽብር ኃይሉ መፈንጫ ሳይሆኑ መቀበሪያ ናቸው❞ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዲኤታ ንጉሡ ጥላሁን