“ኑ! እንዝመት፤ ጠላትን እንደምስስ” ዘማች የመንግሥት ሠራተኞች

167
ሕዳር 14/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በውስጥ እና በውጭ ኀይሎች ቅንጅት በኢትዮጵያ ላይ የተቃጣውን አደጋ ለመመከት የመንግሥት ሠራተኛውም ወደ ግንባር ተምሟል።
በዋግ ኽምራ ግንባር ከዘመቱት መካከል ደግሞ በምሥራቅ በለሳ ወረዳ የአንድ ትምህርት ቤት ርእሰ መምሕር የሆኑት ማዕዛ ተረፈ አንዱ ናቸው። አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኀይል ባለፉት አራት አስርት ዓመታት አማራን በጠላትነት ፈርጆ በግልጽ እና በህቡዕ ግፍና በደል ሲሠራ የቆየና አሁንም ይህንኑ እኩይ ድርጊቱን መኾኑን አንስተዋል።
የመንግሥት ሠራተኛ ማኅበረሰቡን ማገልገል የሚችለው ዘላቂ ሰላም የሰፈነበት ሀገር ሲኖር መኾኑን የገለጹት ዘማቹ ሀገሪቱ ካጋጠማት ችግር መሻገር የሚቻለው በአንድነት ነው ብለዋል።
በቅንጅት በመፋለም የሽብር ኃይሉን መደምሰስ ይገባል ነው ያሉት። ይህንን ለማድረግ ደግሞ የመንግሥትን የክተት ጥሪ ተቀብለው ዋግ ላይ ተገኝተዋል። ደመወዛቸውንም ለሕልውና ዘመቻው መስጠታቸውን ነግረውናል።
ሌላኛው የምሥራቅ በለሳ ዘማችና የትምህርት ቤት ርእሰ መምሕር አቶ ሙላት ይደግ እንዳሉት የመማር ማስተማር ሂደቱን በሰላም ለማስቀጠል የሰላም ጸር የኾነውን የሽብር ኃይል መደምሰስ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው።
አሸባሪውን ኃይል ይፈጽም የነበረውን እኩይ ድርጊት በተማሪነት ዘመናቸው ጀምሮ መረዳታቸውን ያነሱት ዘማቹ ርእሰ መምሕር ዳግም በወራሪው እና አሸባሪው ኀይል በባርነት ቀንበር ሥር ላለመውደቅ የሚደረገው የህልውና ትግል ጊዜው አሁን በመኾኑ ግንባር መዝመታቸውን ገልጸውልናል።
ሌላው የምሥራቅ በለሳ ወረዳ ንግድ እና ገብያ ልማት ጽሕፈት ቤት ባለሙያ ገብሬ አማረ እንደተናገሩት ሕዝብን ማገልገል የሚቻለው በአማራ ሕዝብ ላይ የተቃጣውን የሕልውና አደጋ መመከት ሲቻል ነው። የአማራ ሕዝብ ግድያ፣ መፈናቀል እና የሀብትና ንብረት ውድመት ያስቆጫቸው አቶ ገብሬ የሽብር ኃይሉን ፊት ለፊት ለመፋለም ወደ ግንባር ዘምተዋል። ወራሪውን ኃይል እስከመጨረሻው ለመፋለምም መዘጋጀታቸውን ነው የነገሩን።
በምሥራቅ በለሳ ወረዳ የቀበሌ የግብርና ባለሙያዋ ማርየ ተስፋየ ኢትዮጵያ ያጋጠማትን የውስጥ እና የውጭ አደጋ በጋራ ታጥቆ መመከት እንደሚገባ ገልጸዋል።
ባለፉት የታሪክ ኹነቶች ላይ ሴቶች ያሳዩትን አኩሪ ገድል ለመድገም የክተት ጥሪውን ተቀብለው ወደ ግንባር መዝመታቸውንም ነው የነገሩን። ከዚህ በፊትም በሳህላ ግንባር መዝመታቸውን አስረድተዋል።
“ሀገር ያለ ሰው ምንም ነገር ነው” ያሉት ባለሙያዋ የሽብር ኃይሉ በአማራ ላይ እየፈጸመ ያለውን ግፍ ለመቀልበስ በየግንባሩ “ኑ! እንዝመት፤ እንመክት” በሚል ሠራዊቱን እያበረታቱ ይገኛሉ። በአጭር ጊዜ ጠላትን ለማጥፋት አቅም ያለው ሁሉ ሊዘመት እንደሚገባ ነው የገለጹት።
ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሠራ
ተነሳ!!
መሪህን ተከተል!!
ሀገርህን አድን!!
ነፃነትህን አትስጥ !!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የመዝመት ውሳኔ በኋላ…
Next articleአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል በአዲስ አበባ እና በዙሪያው ለሽብር ተግባር ያሰማራቸው ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ።