ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የመዝመት ውሳኔ በኋላ…

297
አቶ ክርስቲያን ታደለ
የአብኑ አመራር እና የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ክርስቲያን ታደለ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር እንደሚዘምቱ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።
አቶ ክርስቲያን “ለሀገር አንድነትና ለሕዝብ ደኅንነት የምንሰስተው ሕይወት የለምና እኛም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር እንዘምታለን። ሕዝቤ ሆይ ተከተል “ሲሉ ነው በገጻቸው ላይ ያሰፈሩት።
አቶ ነዓምን ዘለቀ
“ለወገን ኢትዮጵያውያን ሁሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን ውሳኔና ጥሪ በመከተል፣ ብዙ ሺህ የቀድሞ ሠራዊት መኮንኖችና ወታደሮች ጋር በመሆን እኔም እዘምታለሁ። ድጋፍና ጸሎታችሁ አይለየን፣ ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር! የወያኔን አራዊታዊ መንጋ እናሸንፋለን” ሲሉ ዘመቻውን ለመቀላቀል ወስነዋል።
አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ
አትሌቱ ሀገሩን ለመታደግ ወደ ግንባር ለመዝመት መወሰኑን አስታውቋል።
“የጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሳኔ ትክክል ነው ያለው አትሌት ፈይሳ በዚህ ወቅት በሀገራችን ላይ የተቃጣውን ችግር ልክ አባቶቻችን በዓድዋ እንዳደረጉት እኔም በግንባር ሄጄ የሚጠበቅብኝን እወጣለሁ” ብሏል።
ያለ መስዋእትነት ድል አይገኝም!
ነፃነትህን አትስጥ!
ተዋርዶ ከመኖር በክብር መሞት ይሻላል!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“ሠንደቁን ሊያጠፉ የከጀላቸው፣ እልፍ ሆኖ ደረሰ ከደጃቸው”
Next article“ኑ! እንዝመት፤ ጠላትን እንደምስስ” ዘማች የመንግሥት ሠራተኞች