
ባሕር ዳር፡ ሕዳር 13/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአሜሪካ ምክር ቤት አባል የሆኑት ሴናተር ሼላ ጃክሰን ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች በአሜሪካ ሂውስተን ቴክሳስ ባካሄዱት የ#NOmore” ንቅናቄ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተገኝተው ከኢትዮጵያ ጎን እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል።
ሴናተሯ በዚህ ሰልፍ ላይ ባደረጉት ንግግር በዴሞክራሲያዊ መንገድ ከተመረጠው የኢትዮጵያ መንግስት እና ከኢትዮጵያዊያን ጎን እቆማለሁ ሲሉ ቃል ገብተዋል።
ኢትዮጵያዊያን በሀገራቸው ላይ እየተደረገ ያለውን ጣልቃ ገብነት ያወገዙበትን ሰልፍ የተቀላቀሉት ሴናተሯ፤ አሸባሪው ትህነግ ሀገር ለማፍረስ በግልጽ ተናግሮ ወረራ እየፈጸመ መሆኑ እየታወቀ በአሜሪካን መንግስት ሳይቀር ድጋፍ መደረጉ አግባብነት የለውም የሚለውን የሰልፈኞቹን የተቃውሞ ድምጽ በአሜሪካን ምክር ቤት እንደሚያሰሙ ሴናተሯ ለሰልፈኞቹ አረጋግጠዋል።
ኢትዮጵያ የጥቁር አፍሪካውያን የባህል ማዕከል መሆኗን ሊታወቅ እንደሚገባ የጠቀሱት ሴናተሯ፤ የአድዋ ድል ለአፍሪካዊያን ምን ማለት እንደሆነ በንግግራቸው አስታውሰዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ