
ሕዳር 12/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በእስራኤል የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያን አንዳንድ ምዕራባውያን ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉት ጫና እንዲያቆሙ እያካሄዱ ባሉት ሰላማዊ ሰልፍ ጠይቀዋል፡፡
እስራኤል ለኢትዮጵያ መንግሥት የምትሰጠውን ድጋፍ አጠናክራ እንድትቀጥልም ሰልፈኞቹ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በኢትዮጵያ ጉዳይ ጣልቃ መግባት ይቁም ፣ በሐሰት መረጃ የሚነዛው ውዥንብር ይቁም ፣ በኢትዮጵያ ላይ የሚካሄደው የማዕቀብ ዘመቻ ይቁም የሚሉና ሌሎች መልዕክቶች በሰልፉ ላይ እየተላለፉ መሆኑን በእስራኤል የኢትዮጵያ ኤምባሲ የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ