በአሜሪካ ዳላስ ቴክሳስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ፡፡

187
ሕዳር 12/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ነዋሪነታቸውን በአሜሪካ ዳላስ ቴክሳስ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል ለተፈናቀሉ ወገኖች ለሁለተኛ ጊዜ 305 ሺህ ዶላር ድጋፍ ማድረጋቸውን አምባሳደር ፍጹም አረጋ አስታውቀዋል፡፡
በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳመላከቱት የተደረገው ድጋፍ ካሁን ቀደም ከተደረጉት ድጋፎች ከፍተኛው ነው፡፡ በድጋፍ ማሰባሰቡ በመሪነት ሚና አበርክቷቸውን ለተወጡት አርቲስት ተስፋዬ ሲማ እና ድጋፍ ላደረጉ ኢትዮጵያውያን አምባሳደሩ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleድሮም በጦርነት ላይ ቀድሞ የሚሞተው እውነት ነው ግን አይቀበርም…
Next articleበእስራኤል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አንዳንድ ምዕራባውያን ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ እያደረጉ ያሉትን ጫና በመቃወም ሰልፍ እያካሄዱ ነው፡፡