
አዲስ አበባ: ሕዳር 12/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸውም ❝በኢትዮጵያ እና በውጭ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ፣ እውነትን ለዓለም ለመግለጥ እያደረጋችሁ ያላችሁት ተጋድሎ እጅግ የሚደነቅ ነው❞ ብለዋል።
❝ይህ ጥንታዊ ሕዝብ ከሩቅ እና ከቅርብ ኃይሎች የተጋረጠበትን የህልውና ስጋት አንድ ሆነን ማሸነፍ እንችላለን። እንደ ዓድዋ ልጆች ኢትዮጵያን በጽናት ወደፊት እናሻግራለን❞ ነው ያሉት።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ