ሂድ በጀግንነት የወንድምህን እና የሀገርክን ጠላት ደምስስ፡፡

189
ደብረታቦር፡ ሕዳር 10/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ወይዘሮ ማሬ በላይ ይባላሉ። ቤተሰባቸውን የሚያስተዳደሩት በመንግሥት ሥራ ሲኾን ነዋሪነታቸው በላይ ጋይንት ወረዳ ነፋስ መውጫ ከተማ ነው። ባንዳነትን ከአያቶቻቸው የወረሱ የፋሽስት ተረክ ውላጆች መርገምትን የጽድቅ ያህል ቆጥረው ጠብተው ያደጉበትን ጡት እየነከሱ ዕልፍ እናቶችን አስለቅሰዋል። ሕዝብን በጠላትነት ፈርጀው ሊያጠፉ አሰፍስፈዋል፤ ኢትዮጵያውያን በደምና በአጥንታቸው የገነቧትን ሀገር ለማፍረስ ሲንቀሳቀሱም በነፋስ መውጫ ሕዝብ ላይ ታሪክ ይቅር የማይለው ጠባሳ ጥለዋል።
ወይዘሮ ማሬ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኀይል ወረራ በፈጸመ ጊዜ የጥፋት በትሩን በቀጥታ ካሳረፈባቸው እናቶች መካከል አንዷ ናቸው። እንደ እናትም እንደ አባትም ሆነው ለብቻቸው ያሳደጉትን የ23 ዓመት ልጃቸውን በግፍ ገድሎ ለመከራ ዳርጓቸዋልና። በደረሰባቸው በደል ልባቸው ተሰብሮ እንዲቀር አልፈቀዱም፤ አንገታቸውን ከመድፋት ይልቅ በቻሉት አቅም የልጃቸውን ደመኛ ለማጥፋት እየተንቀሳቀሱ ነው።
ግንባር ዘምቶ የመዋጋት ፍላጎት ቢኖራቸውም አቅማቸው ስለገደባቸው ቀሪ ብቸኛ ወንድ ልጃቸውን ግንባር ተሰልፎ እንዲዋጋ፣ ማንነቱን እንዲያስከብር ፈቅደዋል። እሳቸው ደግሞ ስለ ኢትዮጵያ እና ሕዝቦቿ ግንባር ለተሰለፈው መከላከያ ሠራዊት፣ ለአማራ ልዩ ኀይል፣ ሚሊሻ እና ፋኖ ስንቅ አዘጋጅቶ በማቅረብ ሥራ ተሰማርተዋል።
ደማቸውን አፍስሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው፣ ስጋቸውን ቆርሰው በብዙ ፈተናዎች ሀገርን ለማጽናት በዱር በገደሉ ለሚዋደቁ መከታዎች ስንቅ ማቅረብ ቀላሉ አስተዋጽኦ ነው ይላሉ ወይዘሮ ማሬ። የስንቅ ድጋፉ የትግሉ አካል በመሆኑ ጠላትን ለማጥፋት እስከመጨረሻው አቅማቸው የፈቀደውን ሁሉ ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማይሉ ተናግረዋል።
በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ ሴት የመንግሥት ሠራተኞች ስንቅ እያዘጋጁ እያቀረቡ ነው። በተለይ ከጥቅምት 1/2014 ዓ.ም ጀምሮ ባለሀብቶችን አስተባብሮ የመሥሪያ ቁሳቁስ በማሟላት ከሕዝብ የተሰበሰበ ሀብትን በማብሰል ነው ግንባር ድረስ እያቀረቡ ያሉት። ጠንካራ ደጀንነታቸውን አጠናክረው ሲቀጥሉም ጦርነቱ እንዲፋጠን እና የአሸናፊነት ግባቸው እንዲሳካ በማሰብ ነው።
“ጦርነቱ በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅ እንፈልጋለን፣ ድጋፋችንም እስከመጨረሻው ይቀጥላል” ብለዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ጊዜያዊ ሎጂስቲክ አስተባባሪዋ የሺዬ መንግሥት እንዳሉት የመንግሥት ሠራተኞቹ በየዕለቱ እስከ ሦስት ኩንታል ዳቦ ቆሎ፣ ከ2 ሺህ 500 በላይ እንጀራ፣ ዳቦ፣ ሽሮ እና ዘይት በመያዝ ነው እስከ ምሽግ ድረስ የሚያቀርቡት። ጦርነቱ እስኪጠናቀቅ ድጋፉ እንደሚቀጥልም አመላክተዋል።
ሕዝቡ በአንድነት ተነስቶ ጠንካራ አደረጃጀት በመፍጠር ጠላትን ማጥፋት ይኖርበታልም ብለዋል።
በደቡብ ጎንደር ዞን ሁሉም ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች ለዘማቾች ሬሽን እያዘጋጁ ግንባር ድረስ እያቀረቡ ነው። የሚቀርበውን ስንቅ ለመከላከያ ሠራዊት፣ ለአማራ ልዩ ኀይል፣ ሚሊሻ፣ ፋኖ እና የክተት ጥሪውን ተቀብለው ለዘመቱ ሁሉ እንዲዳረስ እየተደረገ ነው።
ዘጋቢ:- ደጀኔ በቀለ – ከጋይንት ጋሸና ግንባር
ወራሪውን ጠላት ደምስስ!
የጀግንነት ታሪክህን ዳግም አድስ!
ነፃነትህን አትስጥ!
ተዋርዶ ከመኖር በክብር መሞት ይሻላል!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleሰው ከምትወቅስ እንደጀግናው ቆርጠህ ተነስ፡፡
Next article“አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኀይል የሚታገለው ሀገርን ለባዳ ለመሸጥ እንጂ ሀገር ለማስተዳደር አይደለም” በማይጠብሪ ግንባር የፋኖ ብርጌድ አዛዥ ሻለቃ ሰፈር መለሰ