
ባሕር ዳር፡ ሕዳር 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ለህልውና ዘመቻው ድጋፍ ግሪክ አቴንስ፣ በጣሊያን ሮምና ቱሪን ከተሞች በተካሄደ የገቢ ማሰባሰቢያ ከ33 ሺህ ዩሮ በላይ ገቢ መሰብሰቡን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደገለጸው በሀገራችን ሰሜኑ አካባቢ በጦርነት እና በተለያዩ አካባቢዎች ለተፈናቀሉት ወገኖቻችን መልሶ ለማቋቋም ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በገንዘብና ባላቸው አቅም ድጋፍ አድርገዋል።
ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በተደረገው ጥሪ መሰረት ሮም የኢፌዴሪ ኤምባሲ በሚሸፍናቸው አካባቢዎች በግሪክ ሀገር በአቴንስ ከተማ፣ በጣልያን ሀገር ሮምና ቱሪን ከተሞች በዚህ ሳምንት ለሦስተኛ ጊዜ የገንዘብ ማሰባሰቢያ መርሃግብር ተካሂዷል።
በዚህም አጠቃላይ 33 ሺህ 482 ዩሮ ተሰብስቦ በአስተባባሪ ኮሚቴዎች አማካኝነት ዛሬ ገቢ መደረጉን ኢዜአ ዘግቧል።
ወራሪውን ጠላት ደምስስ!
የጀግንነት ታሪክህን ዳግም አድስ!
ነፃነትህን አትስጥ!
ተዋርዶ ከመኖር በክብር መሞት ይሻላል!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ