በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች በተካሄደው ኦፕሬሽን በመቶዎች የሚቆጠሩ የሸኔ አሸባሪዎች ሲደመሰሱ በርካቶች ደግሞ ተማርከዋል።

341
ባሕር ዳር፡ ሕዳር 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ከጥቅምት 2 እስከ ህዳር 8/ 2014 ዓ.ም በፌዴራል ፖሊስ፣ በኦሮሚያ ልዩ ኀይልና ሚሊሻ በጋራ በተካሄደው ኦፕሬሽን በተለያዩ የዞኑ ወረዳዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የአሸባሪው ሸኔ ቡድን አባላት ተደምስሰዋል።
በምዕራብ ሸዋ ስር በሚገኙ በዳኖ እና ጅባት ወረዳዎች 63 ታጣቂዎች፣ በአምቦ ወረዳ 47፣ በአቡነ ግንደ በረት 235፤ በጥቅሉ 345 ታጣቂዎች ርምጃ ተወስዶባቸዋል። ከእነዚህ ውስጥ አራቱ የአሸባሪው የጦር መሪዎች መሆናቸው ታወቋል።
በርካታ ቁጥር ያለው የአሸባሪው የሸኔ ኀይል ቁስለኛ የሆነ ሲሆን በርካቶችም እጃቸውን ለፀጥታ አካላት ሰጥተዋል። ከዚህም በተጨማሪ በርካታ የጠላት ቡድኑ ሰርጎ ገቦችና ሰላዮች ተይዘዋል።
ሰላማዊ መስለው በኅብረተሰቡ ውስጥ ለመደበቅ የሞከሩ የአሸባሪው የሸኔ አባላት በሕዝቡ ጥቆማና ከፍተኛ ተሳትፎ እየተለቀሙ እንደሚገኙ
የመየመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል።
ወራሪውን ጠላት ደምስስ!
የጀግንነት ታሪክህን ዳግም አድስ!
ነፃነትህን አትስጥ!
ተዋርዶ ከመኖር በክብር መሞት ይሻላል!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየተጀመረው የኢትዮጵያ ትንሳኤ ጉዞ ዳር ሊደርስ ተቃርቧል።
Next article“ዳጉ” የሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይልን የሐሰት ፕሮፓጋንዳን ከመመከት አልፎ እንቅስቃሴውን በማክሸፍ የጎላ አስተዋጽኦ እያደረገ ነው