አሸባሪዉን የትግራይ ወራሪ ኀይል ሴራ ለመቀልበስ ኢትዮጵያዉያን በጋራ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸዉን የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

159
አዲስ አበባ፡ ሕዳር 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸዉ የህልዉና ዘመቻዉን ለመደገፍ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ፣ የደቡብ ክልል ደግሞ ከ270 ሽህ ብር በላይ ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን ሌሎች ክልሎችም ይህንን የህልዉና ዘመቻ ለማሳካት የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን አንስተዋል።
በህልዉና ዘመቻዉ በግንባር ለመሠለፍ እና መከላከያ ሠራዊትን በሰዉ ኀይል ለማጠናከር በሽዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ወደ ስልጠናዉ መቀላቀላቸዉንም ሚኒስትሩ ዶክተር ለገሰ ገልጸዋል።
አመራሮችም የደጀንነት ሥራዎችን ከመሥራት ባለፈ በግንባር በመሰለፍ እየተፋለሙ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ሕረብረተሰቡ ከጸጥታ አካላት ጋር በመሆን ባደረገው ፍተሻ ሕገወጥ የጦር መሳሪያዎች እየተያዙ መሆኑንም አንስተዋል። በግለሰብ ቤቶችና እና በጅምር ህንፃዎች ዉስጥ ሕገወጥ ገንዘብ እና የጦር መሳሪያዎች እየተገኙ ነዉ ብለዋል። በፍተሻ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአፋር ልዩ ኀይል ጣቃ ልብስ መገኘቱንም ገልጸዋል፡፡
ዘርን መሠረት ያደረገ የእስር ሂደት እየተከናወነ ነዉ ተብሎ እየተናፈሰ ያለዉ መረጃ የተሳሳተ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሩ ከኦነግ ሸኔ እና ከአሸባሪው ትህነግ ጋር ግንኙነት ያላቸዉን አካላት ብቻ የማሰር እና የማጣራት ሥራ እየተከናወነ ነዉ ብለዋል።
በወረኢሉ እና በሚሌ ግንባር ያለዉ የአሸባሪው ኀይል በወገን ጦር መመታቱንም አስታውቀዋል። የሽብር ኀይሉ አባላት በዚህ ዉጊያ ተገድለዋል፣ ተማርከዋል፣ ቆስለዋል ነው ያሉት።
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኀይል ሚሌን ያዝኩ በማለት ሀሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭ መቆየቱን ተናግረዋል። እውነታው ግን አሸባሪው ኀይል በመደምሰስ ላይ ነው ብለዋል።
ዘጋቢ:–ማህሌት ተፈራ– ከአዲስ አበባ
ወራሪውን ጠላት ደምስስ!
የጀግንነት ታሪክህን ዳግም አድስ!
ነፃነትህን አትስጥ!
ተዋርዶ ከመኖር በክብር መሞት ይሻላል!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleአሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ኃይል ከምድረ ገጽ በማጥፋት ሕዝብ ወደ ሰላማዊ ሕይዎቱ እንዲመለስ እንደሚያደርጉ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት ገለጹ፡፡
Next articleፋኖ ሠንደቁን አስቀድሞ እየገሰገሰ ነው!