አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ኃይል ከምድረ ገጽ በማጥፋት ሕዝብ ወደ ሰላማዊ ሕይዎቱ እንዲመለስ እንደሚያደርጉ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት ገለጹ፡፡

639

ሕዳር 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ጀግናው የአማራ ልዩ ኃይል ጠላትን እያስጨነቀ እየደመሰሰ ነው። በሚሰጠው ግዳጅና አውደ ውጊያ ሁሉ በድል ላይ ድል እየጨመረ ጠላትን ወደ ተመኘው ሲኦል እየሸኘው ነው።

ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ቆይታ ያደረጉት በወሎ ግንባር የአማራ ልዩ ኃይል አባላት በአጭር ጊዜ ውስጥ ሽብርተኛውን የትግራይ ወራሪ ኃይል ሙሉ በሙሉ አጥፍተው ሀገርና ሕዝብን እፎይ እንደሚያስብሉ አረጋግጠዋል። አባላቱ እንደገለጹት ልዩ ኃይሉ በተለያዩ አውደ ውጊያዎች ላይ ተሳትፎ በማድረግ አስደናቂ ጀብዱዎችን እየፈጸመ ነው።
በገቡበት አውደ ውጊያ ሁሉ አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ኃይል እየቀበሩት እንደሆነ ነው የተናገሩት። አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል በሐሰት እንደሚነዛው ሳይሆን ባረጀ እና ባፈጀ የውጊያ እና የፕሮፖጋንዳ ስልት ሕዝብ እንደሚረብሽ የገለጹት አባላቱ ግንባር ላይ ያለው እውነታ ግን ተቃራኒ ነው ብለዋል፡፡
በገፍ የሚያመጣው ወራሪ ኀይል በጀግናው የአማራ ልዩ ኃይል እንደሚደመሰስ በመግለጽ፡፡ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል ከምድረ ገጽ እስኪጠፋ እየደመሰሱት እንደሆነ ገልጸው አማራ ብሎም ኢትዮጵያ ከሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይል በቅርቡ ነጻ ይወጣሉ ብለዋል፡፡ ሕዝቡም አንገቱን ቀና አድርጎ በነጻነት እንዲንቀሳቀስ እንደሚያደርጉት ቃል በመግባት።
አባላቱ ይህን በእርግጠኝነት ነው የምንናገረው፤ በእርግጠኝነት ድል ከእኛ ጋር ነው ብለዋል። በግንባሩ የአንድ የሻምበል አዛዥ እንደነገሩን ጀግናው የአማራ ልዩ ኃይል በርካታ ግዳጆችን በድል እየተወጣ ነው፤ በአንድ አውደ ውጊያ ብቻ ጠላት በዘጠኝ ሲኖ ትራክ አስከሬኑን ይዞ እንዲሸሽ ማድረጋቸውን ለአብነት አንስተዋል።
በርካታ ምሽጎቹን በመስበር፣ ጠላትን በመደምሰስ አስደናቂ ጀብዱዎችን ሲፈፅሙ መቆየታቸውንም ነግረውናል። አዛዡ እንዳሉት ጀግናው የአማራ ልዩ ኃይል የአሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ኃይል ከባድ መሳሪያዎች ከጥቅም ውጭ በማድረግና በማቃጠል ሀገር የማፍረስ ቅዠቱን እያከሸፉበት ነው፡፡
“ሕዝባችንን ከጎናችን አሰልፈን የማንፈፅመው ጀብዱ የለም፤ በሁሉም መልኩ ድል እየተጎናጸፍን ነው” ብለዋል። አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል አማራን እንደ ሕዝብ ለማጥፋት እና ኢትዮጵያን ለማፍረስ አልሞ የተነሳ እኩይ በመሆኑ ሁሉም በህልውና ዘመቻው በመሳተፍ እንዲፋለመው አስታውቀዋል።
አሚኮ ያነጋገራቸው ሴት የአማራ የልዩ ኃይል አባላትም ከወንዶች ባልደረቦቻቸው ጋር ጠላትን እየደመሰሱ መሆናቸውን ተናግረዋል። “ድል እናደርጋለን፤ በገባንበት አውደ ውጊያ ሁሉ እናሸንፋለን፤ ወደ ኋላም ብለንም አናውቅም፤ ጠላትን እንደመስሳለን” ነው ያሉት።
አባላቱ የአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል ከአማራ ክልል ብቻ ሳይሆን ከምድረ ገጽ እስካልጠፋ ድረስ ግስጋሴያችንን አናቆምም ነው ያሉት። ‘የአማራን ሕዝብ እናጠፋለን፤ ኢትዮጵያን እናፈርሳለን’ ያሉትን ሁሉ ምኞታቸውን ባዶ እናደርገዋለን ብለዋል።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
ወራሪውን ጠላት ደምስስ!
የጀግንነት ታሪክህን ዳግም አድስ!
ነፃነትህን አትስጥ!
ተዋርዶ ከመኖር በክብር መሞት ይሻላል!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየወገን ጦር በወረኢሉ እና አካባቢው ባደረሰው ጥቃት ጠላት ከፍተኛ ኪሳራ እንደደረሰበት የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳዳሪ ገለጹ።
Next articleአሸባሪዉን የትግራይ ወራሪ ኀይል ሴራ ለመቀልበስ ኢትዮጵያዉያን በጋራ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸዉን የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።