
ሕዳር 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደሪ አቶ አብዱ ሁሴን በተለይም ለአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) እንደገለፁት በወገን ጦር በኩል በሚሰጠው ስምሪት በጠላት ላይ አስፈላጊው ጥቃት በማንኛውም ጊዜ ማድረስ የሚያስችል አጠቃላይ ዞናዊ ዝግጅት ተፈጥሯል። ለተዋጊው ስንቅና ሌሎች ድጋፎችን ለማድረግ አደረጃጀት ተፈጠሮ በተግባር እየተሠራ ነው ብለዋል።
በተለያዩ አካባቢዎች ሕዝቡ ከወገን ጦር ጋር ኾኖ ጠላትን መመከቱንና አካባቢውን ነጻ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
የወገን ጦር በወረኢሉና አካባቢው ባደረሰው ጥቃት ጠላት ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ እንደደረሰበትም አስታውቀዋል። ጠላት አሁን ላይ ኃይሉን የመሰብሰብና ወደ ሌላ ግንባር የማዞር ተግባር እየፈጸመ መሆኑንም ገልጸዋል።
ጠላት ታሪካዊቷን ቦታ ወረኢሉን ያዝኩ እያለ ያስወራው ወሬ ውሸት መሆኑን አረጋግጠዋል። በግንባሩም ጠላት ከመደምሰስ ውጭ ሌላ ያተረፈው ነገር አለመኖሩንም ገልጸዋል። “የጥንታዊቷን ወረኢሉ ታሪክ ማጠልሸት የአማራን ታሪክና ሥነ ልቦና መስበር አድርጎ ስለሚወስደው በማኅበራዊ ሚዲያ ባሰማራቸው ተከታዮቹ አካባቢውን ያዝኩ እያለ የሚነዛው ወሬ ውሸት ነው፤ እውነታው የሽብር ኃይሉ መደምሰሱ ነው” ብለዋል።
ጠላት ያልያዘውን አካባቢ ያዝኩ እያለ እንደሚያስወራ ያነሱት ዋና አስተዳዳሪው የወረኢሉ፣ ጃማና ለገሂዳ ሕዝብ ከወገን ጦር ጋር በመቀናጀት ጠላትን እየቀበረ መሆኑን አስታውቀዋል።
የአካባቢው ሕዝብ ለወገን ጦር ግንባር ድረስ ዘልቆ ስንቅ እያቀረበ መሆኑንም ተናግረዋል። ሠርጎ ገቦችን ሕዝቡ እርምጃ እየወሰደባቸው መሆኑንም አመላክተዋል።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
ወራሪውን ጠላት ደምስስ!
የጀግንነት ታሪክህን ዳግም አድስ!
ያለ መስዋእትነት ድል አይገኝም!
ነፃነትህን አትስጥ!
ተዋርዶ ከመኖር በክብር መሞት ይሻላል!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ