
ባሕር ዳር፡ ሕዳር 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ወረኢሉን ለመቆጣጠር አስቦ ኃይሉን ሲያሰባስብ የነበረው አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኀይል የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኀይልና ሚሊሻ፣ ፋኖና የአካባቢው ታጣቂ በጋራ በፈጸሙት ጥቃት ተደመሰሰ።

በሺዎች የሚቆጠር አሸባሪ የተደመሰሰ ሲሆን ከፍተኛ የአሸባሪው አመራሮችን ጨምሮ በርካቶች ተማርከዋል።
አሸባሪው ኀይል በዚህ ግንባር ከሕጻን እስከ ሺማግሌ ያሰለፈ ሲሆን ምርኮኞቹም በየአካባቢው ያለው አሸባሪው ኀይል ተስፋ እየቆረጠ መሆኑን ተናግረዋል።
ጀግናዎቹ የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ እና ፋኖ ወደ ፊት እየገሠገሡ መሆኑም ታውቋል።
ወራሪውን ጠላት ደምስስ!

የጀግንነት ታሪክህን ዳግም አድስ!
ነፃነትህን አትስጥ!
ተዋርዶ ከመኖር በክብር መሞት ይሻላል!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ