
በቀጣይም በግንባር በመገኘት ለወገን ጦር የአይነት ድጋፍ እንደሚደረግም ተገልጿል።
ባሕር ዳር: ሕዳር 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ኃይል በግንባር እየተፋለመ ላለው የወገን ጦር የተለያዩ ድጋፎች እየተደረጉ ይገኛሉ፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባሕር ዳር ቅርንጫፍ ሠራተኞች ለህልውና ዘመቻው የአንድ ወር ደመወዛቸውን መለገሳቸው ይታወሳል፡፡ ሠራተኞቹ ከዚህም ባሻገር በተለያዩ ተግባራት በመሳተፍ የዘመቻ ጥሪውን እየደገፉ ይገኛሉ፡፡
በለጠ ሽፈራው የተቋሙ ሠራተኛ ነው። በግንባር ላሉ ጀግኖች ደም ለግሷል፡፡ ደም መለገስ ትንሹ ስጦታ እንደሆነም ተናግሯል፡፡ ደም ከመለገስ ባሻገር ስንቅ በማዘጋጀት እየተሳተፈ እንደሆነ የገለጸው በለጠ ትውልዱ በነጻነት አንገቱን ቀና አድርጎ እንዲቀጥል አሁን ላይ የየድርሻችንን መወጣት አለብን ብሏል፡፡

የተፈናቀሉ ወገኖችንም እየደገፉ መሆኑንም ገልጿል።
ሌላኛዋ ደም ሲለግሱ ያገኘናቸው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባሕርዳር ቅርንጫፍ የሽንብጥ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሶለል ይኸይስ ዘማቾች ህይወታቸውን ሲሰጡ እኛ ደግሞ ደማችንን መስጠት እጅግ ትንሹ አበርክቶ ነው ብለዋል፡፡ በሚጠበቅባቸው ኹሉ ለመደገፍ ዝግጁነታቸውንም ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባሕር ዳር ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ አንማው ወርቅነህ የባንኩ ሠራተኞች የአንድ ወር ደምወዛቸውን መለገሳቸውን ጠቅሰዋል፡፡
በህልውና ዘመቻው ከወገን ጦር ጎን መሆናችንን ለማሳየት የደም ልገሳ አካሂደናል ብለዋል፡፡ ለተከታታይ ጊዜ ደም መለገሳቸውን የገለጹት ሥራ አስኪያጁ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከሠራተኛው 230 ሺህ ብር በማዋጣት ግንባር ደረስ ሄደው ለወገን ጦር ድጋፍ ለማድረግ የተለያዩ አልባሳትን መግዛታቸውን አመላክተዋል፡፡
በባሕር ዳር ደም ባንክ አገልግሎት የደም ልገሳው አስተባባሪ ሲስተር ገነት አስፋው በበኩላቸው የባንኩ ሠራተኞች በተከታታይ ደም እየለገሱ እንደሆነ ገልጸዋል።

ዘጋቢ፡-ደጀን አምባቸው
ወራሪውን ጠላት ደምስስ!
የጀግንነት ታሪክህን ዳግም አድስ!
ያለ መስዋእትነት ድል አይገኝም!
ነፃነትህን አትስጥ!
ተዋርዶ ከመኖር በክብር መሞት ይሻላል!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ