ተምዘግዛጊ ነብሮቹ በወሎ ሰማይ ሥር!

853
ሕዳር 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ጠላቶች የሚፈሩት፣ የሚያከብሩት፣ በግንባሩ የማይጠጉት፣ ወዳጆች የሚኮሩበት፣ የሚመኩበት የጀግኖች ስብስብ፣ በእንቅስቃሴዎች ሁሉ ጠንካራ ሀገር፣ አንዲት ኢትዮጵያን የሚያስብ። ምድር ብትጨነቅ፣ ንውጽውጽታው ቢበዛ፣ ውሽንፍሩ ቢበረክት፣ ጠላት ቢደረደር ልቡ የማይሸበር፣ በአቋሙ የፀና አንድ ኀይል አለ። አንድ ልብ፣ አንድ ዓላማ ያለው፣ ጀግንነት የታደለው። የአተኳኮስ አስተማሪ፣ የድል መንገድ ቀድሞ መሪ፣ ከታሪክ ላይ ታሪክ ሠሪ፣ የጦር ቀመር ቀማሪ፣ አንዲት ሀገር ፅኑ ኢትዮጵያ እያለ ዘማሪ፣ ወገን አኩሪ፣ ጀብዱ ሠሪ።
ከእናት አባት የወረሰውን ጀግንነት፣ ከደም ሥር ጋር የተዋሃደው ኢትዮጵያዊነት፣ መገለጫው የሆነውን አሸናፊነት፣ የፀናውን አንድነቱን አንግቦ ለሠንደቁ ክብር፣ ለሀገር ፍቅር ይዋደቃል። ለኢትዮጵያ ክብር ይዘምታል፣ ለአንድነቷና ለሉዓላዊነቷ ይሞታል፣ በስም የወጣለት ልዩ ኀይል፣ ኢትዮጵያን አትንኳት፣ በክፉ ዓይን አትመልከቷት፣ መከራዋን አታብዙባት፣ ጦር አታዝምቱባት፣ በክፉ አትምከሩባት፣ ክብሯን አትንኩባት፣ ቀየዋን አታርክሱባት ይላል። ለኢትዮጵያ መገፋት፣ መወጋት፣ መከፋት አይሆናትምና። ኢትዮጵያን አትንኳት ብሎ ከነኩበት፣ አትውጓት ብሎ ከወጉበት ቁጣው ይነሳል፣ እንደ አንበሳ ያገሳል፣ ነፍጡን ያነሳል፣ ሀገሩን የነካትን ሁሉ ቀጥቶ ይመልሳል። ለኢትዮጵያ ሲሆን ሞት ይቀላል፣ ለኢትዮጵያ ሲሆን መንገድ ይሰምራል፣ ለኢትዮጵያ ሲሆን ነገር ሁሉ ያምራል።
ለኢትዮጵያ የሞቱት ታሪክ ዘክሯቸዋል፣ በወርቅ ቀለም መዝግቧቸዋል፣ ትውልድ አክብሯቸዋልና ለኢትዮጵያ፣ ስለኢትዮጵያ ሁሉንም ለመቀበል ይነሳል። አትንኳት ያላትን ኢትዮጵያን ነክተዋልና ተቆጥቷል። ኢትዮጵያዊነት ፅናት፣ ኢትዮጵያዊነት ኩራት፣ ኢትዮጵያዊነት ብሥራት፣ ኢትዮጵያዊነት የዘመናት ሁሉ መብራት፣ ኢትዮጵያዊነት የነፃነት ምልክት፣ ኢትዮጵያዊነት ማሸነፊያ፣ ኢትዮጵያዊነት የጭንቅ ዘመን ማለፊያ፣ ኢትዮጵያዊነት የማያረጅ የማይጠወልግ መጎናፀፊያ፣ ኢትዮጵያዊነት የተስፋ ፀሐይ መውጫ፣ ኢትዮጵያዊነት የክብርና የፍቅር መምጫ ነው ይላል። ኢትዮጵያን ብሎ ይዘምታል፣ ኢትዮጵያን ጠርቶ ይማታል፣ ኢትዮጵያን ብሎ ይገሰግሳል፣ ኢትዮጵያን ጠርቶ ምሽግ ያፈርሳል፣ ጠላትን ይደመስሳል።
የአሸናፊነት ምስጢሩ፣ የዘመናት ክብሩ የተቀዳው ከፀና ኢትዮጵያዊነቱ ላይ ነው። ስለ ተከበረው ሕዝብ፣ ስለተቀደሰችው ሀገር ሲል ድሎትን ይረሳል፣ ሕይወቱን በምሽግ ይቀልሳል፣ ለተመቻቸ ሕይወት፣ ለሚመኩበት ኩራት ነፃነት ይቀድማልና ለነፃነት ሲል ሁሉን ይሰጣል። የሚቆጥበው የለውም። በኢትዮጵያ ምድር የሚፈስሰው የጀግንነት ወንዝ ዛሬም አልደረቀም፣ እንደ ትናንቱ ዛሬም ያፈልቃል፣ የተጠሙትን አጠጥቶ ያረካል፣ የጀግንነቱ ወንዝ፣ የአሸናፊነቱ ጅረት ዛሬም ከኢትዮጵያ ምድር እየፈለቀ ነው። ከዘመን ዘመን እየገነነ የሚሄድ ጀግንነት፣ ከጊዜ ጊዜ እየጎመራ የሚወጣ አሸናፊነት በኢትዮጵያ ምድር ሞልቷል። ከትናንት ወዲያ የፈለቁት ሀገር አስከብረው፣ ጠላት አሳፍረው፣ የክብር ሞት ሞተዋል። ትናንት የፈለቁትም እንደ ቀደሙት አድርገዋል። ዛሬ የፈለቁትም ሀገር ለማስከበር እየተዋደቁ ነው። የወረሱት አሸናፊነት ብቻ ነውና ጉዟቸውን በአሸናፊነት ይቋጫሉ፣ ትግላቸውን በድል አድራጊነት ይደመድማሉ፣ የወረሱትን አሸናፊነት ነገ ለሚፈልቀው ያወርሳሉ።
ኢትዮጵያውያን ለልጆቻቸው የሚያወርሱት፣ ለተከታዮቻቸው የሚያለብሱት የአሸናፊነትን ጦር፣ የአሸናፊነትን ምስጢር፣ የአሸናፊዎችን ሀገር ነው። ለኢትዮጵያ የሆነ ሞት ዘላለማዊነት ነው። አረንጓዴ ብጫ ቀዩን ሠንደቅ ከፊት አስቀድሞ የዘመተ ሁሉ በድል አድራጊነት ተመልሷል። በዘመናት ትምህርት ቤት እንደ ኢትዮጵያ የተፈተነ እንደ ኢትዮጵያም ሁሉንም በብቃት ያለፈ ያለ አይመስልም። ፈታኞቿ ሁሉ ከሚጠብቋት ልጆቿ እና ከሚጠብቃት ፈጣሪዋ በታች ናቸው። እርሷ የፈተነች ጊዜ አላፊ አይኖርም፣ እርሷ የተነሳች ጊዜ ቋሚ አይኖርም። በአንድነት ስትነሳ በደለኞች ይወድቃሉ፣ ክፉዎች ይረግፋሉ፣ በሰበቁት ጦር ተወግተው ያልቃሉ።
በወሎ ሰማይ ስር ነኝ። ከጀግኖች መካከል፣ በጀግኖች ተከብቤ። በተምዘግዛጊ ነብሮቹ በአማራ ልዩ ኀይል። የጀግኖቹ ሁሉ ነገር ማርኮኛል። ልቤ እስኪጠፋ ድረስ ስቦኛል። በስስት ተመለከትኳቸው። ያሳሳሉ። ከእነርሱ ጋር ለሆነ ሁሉ ያኮራሉ። አንድነት፣ ፅናት፣ ቁርጠኝነት፣ አይበገሬነት ይታይባቸዋል። በአግራሞት ተመለከትኳቸው። ትጥቃቸውን አጥብቀው ተዘጋጅተዋል። የልባቸው ሙላት፣ የለበሱት ኩራት ፊታቸው ላይ ይነበባል።
ቀልቤ እንደተሳበ ከተምዘግዛጊ ነብሮቹ መካከል አንደኛው አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን ሠንደቅ ይዞ ከመቀመጫው ተነሳ። ወኔ በተላበሰ ድምፁ ሠራዊቱን ያስጨፍረው ጀምር። “አማራ አማራ ነው፣ ወያኔ ሌባ ነው” ከተምዘግዛጊ ነብሩ የወጣው የመጀመሪያው ስንኝ ነው። ተምዘግዛጊ ነብሮቹ ተቀብለው “አማራ አማራ ነው፣ ወያኔ ሌባ ነው” እያሉ አስተጋቡት። አግራሞቴ የበለጠ ጨመረ። በትኩረት ማዬቴን ቀጠልኩ። አዎን አማራ የኮራ አማራ ነው። ወያኔ ግን ሌባ፣ ዘራፊ፣ ሀገር ሻጭ ነው። “ከእንግዲህ አማራን የሚነካው ማነው፣ እየተደራጀ እየታጠቀ ነው” ተምዘግዛጊ ነብሩ ቀጥሏል። ጭፈራው ደራ፣ አዎን አማራን የሚነካው የለም።
ኢትዮጵያንም የሚደፍራት አይኖርም። ከአንበሳ የጀገኑ፣ ከነብር የፈጠኑ፣ እያነጣጠሩ የሚጥሉ፣ በተኮሱት ልክ ግዳይ የሚቆጥሩ ጀግኖች እያሉ፣ ለዛውም ታጥቀው፣ ተመርቀው፣ ቆርጠው ተነስተው ማንም አይነካውም። ልክ ብሏል ጀግኖች እያሉ ማንም ሊነካው አይችልም። በአፈሙዛቸው እየተበላ ያልቃል እንጂ። አዎን ጀግኖቹ አማራን ታላቋ ኢትዮጵያን ያስከብሯታል። አማራውም እየተደራጄ እየታጠቀ ጠላት ወደሚገኝበት ተሟል እና የሚነካው የለም። እኔም ግርምቴ ጨምሯል። እነርሱም በስሜት ጭፈራቸውን ቀጥለዋል።
“ገደል ለገደል ይሄዳል ዝንጀሮ፣
በአማራው መጥተሃል ቁርጥ ነው ዘንድሮ” በአማራነት፣ በኢትዮጵያዊነት መጥቷልና የቁርጥ ቀን ነው። በማይመጣው ስለመጣ ጀግኖቹን አስቆጥቷል። ሕዝብን በብስጭት አስነስቷል። አካባቢው ደመቀ፣ ስሜታቸው የበለጠ ሞቀ። ማን ሊደፍራት የእነርሱን ሀገር፣ ማንስ ሊኖር በእነርሱ መንደር፣ ምለው ተነስተው፣ ነፍጣቸውን አንስተው። ማንስ ነው ከፊታቸው የሚቆመው? እውነትም ኢትዮጵያ ማሕፀነ ለምለም ነሽ። ጀግና የሚበቅልብሸ፣ ጎበዝ የሚፈልቅብሽ፣ ትውልድ የሚኮራብሽ፣ ታሪክ የሚያከብርሽ፣ ከፍ አድርጎ የሚያስቀምጥሽ፣ በማይጠፋ ብዕር የሚቀርፅሽ፣ በማያረጅ ብራና የሚያሰፍርሽ። ተመዝግዛጊ ነብሮቹ ቃል ኪዳን አስረዋል፣ የእናት አባት ታሪካዊ አደራ ተቀብለዋልና በጀግንነት ቆርጠው ተነስተዋል።
“መጣችሁ ወልቃይት ገባችሁ ጠገዴ፣
ይሄው ቀመሳችሁ በረጃጅም ጓንዴ፣
የትግራይ ታጣቂ አዎይ መከራው
ደብረ ፅዮን ዋሽቶ ሊያስገድለው ነው።
አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ሠንደቃችን፣
በአንድነት በፍቅር መተሳሰሪያችን፣
በክላሽም መሞት፣ በአብራራውም መሞት ሞት አይምሰላችሁ፣
የሞት ሞቱንማ እኔ ልንገራችሁ፣
እምዬ ኢትዮጵያን ጠላት ሲቀማችሁ” እያለ ተምዘግዛጊው ነብር ጭፈራውን አደመቀው። በእጁ የጨበጣት፣ ከደሙ ጋር ያዋሃዳት፣ ቃል ኪዳኑን ያሰረባት፣ አደራ የተቀበለባት አረንጓዴ ቢጫ ቀዩዋ ሠንደቅ ተውለበለበች። ከፍ ከፍም አለች። ለከፍታ የተመረጠች፣ ምልክት የሆነችናትና ከፍ አለች።May be an image of 2 people, people standing and outdoors
“አይዞሽ እናት ሀገሬ
አይዞሽ ኢትዮጵያ ሀገሬ
ባንዲራሽ ከፍ ይበል ዛሬ” እያለ የበለጠ ከፍ አደረጋት፣ ወደ ላይ ሰቀላት፣ ከፍ አድርጎ አከበራት። “እኛ ለባንዲራ እንሞታለን ገና፣ ለእናት ሀገራችን ይፈሳል ደማችን” ቃል ኪዳኑን በጋራ አሠሩት። ነገም አላሉም፣ ከነገ ወዲያ ብለውም አልቀጠሩም። ደማችን ዛሬ ይፈስልሻል። አጥንታችን ዛሬውኑ ይከሰከስልሻል እያሉ ማሉላት።
የወሎ ሰማይ ሥር በተምዘግዛጊ ነብሮቹ ደመቀች፣ ምድር ተጨነቀች፣ ነብሴ በሀሴት ተሞላች፣ በእጁ ጨብጦ ከሚያውለበልባት ሠንደቅ ጋር ከነፈች። ለካስ ለክብር ሲነሱ ስሜቱ እንደዚህ ነው። ወኔው ኀያል ነው። ከፍ ብላ የተሠቀለችውን ሠንደቅ ለዘላለም ከፍ ሊያደርጓት፣ የሚጥሩባትን አሸናፊነትን ብቻ ሊሸልሟት በፊቷ ማሉላት።
“አንበሳው አንበሳው የአማራው ነበር፣
እንሞታለን እንጂ አንሰጥም ሀገር” አዎን ሀገር መስጠት በዘራቸው የለም፣ በደምና በአጥንት የፀናች ሀገር ለትውልድ ማውረስ ነው ታሪካቸው። የወሎ ሰማይ ሥር በጀግኖቹ ወኔ ደመቀች። እኔም በስስት ተመለከትኳቸው። ጀግኖቹ አሁን የሕዝብና የሀገር ጠላት የሆነውን የትግራይ ወራሪና አሸባሪ ቡድንን እንደሚያጠፉት እርግጠኞች ናቸው። የአማራ ሕዝብ ብሎም መላው ኢትዮጵያውያን በእነርሱ ጀብዱ እንደሚኮራም ነግረውኛል። የአባቶቻችን ልጆች መሆናችን እናሳየዋለን ብለውኛል። ባየሁት ሁሉ ደስ ብሎኛል። መንፈሴ መልካም ነገርን ገብይቷል፣ ዓይኔ ጀግኖቹን ተመልክቷል፣ ጀሮዬ የጀግኖችን ድምጽ ሰምቷል።May be an image of 1 person and outdoors
አንተም ጀግኖችን አይዞህ በላቸው፣ ትጥቅና ስንቅ አቀብላቸው፣ ያን ጊዜ ደማቅ ታሪክ ሠርተው ያሳዩሃል። በወሎ ሰማይ ሥር ተምዘግዛጊ ነብሮቹ ይደምቁበታል፣ ጠላትን ይቀጡበታል።
በታርቆ ክንዴ
ወራሪውን ጠላት ደምስስ!
የጀግንነት ታሪክህን ዳግም አድስ!
ነፃነትህን አትስጥ!
ተዋርዶ ከመኖር በክብር መሞት ይሻላል!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article❝የጠላትን ግፍ ለመጨረሻ ጊዜ ለማስቆም መከፈል የሚገባውን መስዋእትነት እንከፍላለን❞ የአማራ ሳይንት ሚሊሻዎች
Next articleበኩር ጋዜጣ ሕዳር 06/2014 ዓ.ም ዕትም