
ሕዳር 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትግራይ ኃይል በአማራ ክልል በፈጸመው ወረራ በደሎችን እየፈፀመ ነው። ወረራ በፈፀመባቸው አካባቢዎች ንጹሐንን ገድሏል፣ አፈናቅሏል፣ ሀብትና ንብረት ዘርፏል፣ አሁንም ወረራ በፈፀመባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች የግፍ ግፍ እየተፈፀመባቸው ነው። የዜጎችን በደል ለማስቆምና የተወረሩ አካባቢዎችን ነፃ ለማውጣት መንግሥት የክተት ጥሪ ማስተላለፉ ይታወሳል። በተላለፈው የክተት ጥሪ መሠረት ጀግኖች ወደ ጦር ግንባር እየተመሙ ነው።
በደቡብ ወሎ ዞን የአማራ ሳይንት ወረዳ ሚሊሻዎችም ጠላትን በገበባት ለማስቀረት ግንባር ገብተዋል። ሃምሳ አለቃ አዛናው ሹመት በሀገር መከላከያ ሠራዊት ለአሥር ዓመታት አገልግሏል። በቆዬባቸው ጊዜያትም ኢትዮጵያ የሰጠችውን ግዳጆች በብቃት ተወጥቷል። አሁን ላይ ደግሞ በአማራ ሳይንት ወረዳ በዘማች ሚሊሻ ውስጥ እየሠራ ነው።
ከአሚኮ ጋር በነበረው ቆይታ እንዳለው ጠላትን ለመደምሰስ የተሰጣቸውን ግዳጅ በጥሩ ሁኔታ እየተወጡ ነው። አሁንም የተሰጣቸውን ግዳጅ በብቃት እንደሚወጡት ነው የተናገረው። የሳይንት ነዋሪ የታጠቀ ነው ያለው ሃምሳ አለቃ ለጠላት እጅ የሚሰጥ የለም፣ እናሸንፋለንም ብሏል። ሚሊሻው ለየትኛውም ትግል ቆራጥ መሆኑንም ገልጿል።
በአማራ ሳይንት ኹሉም ዘምቶ ለመዋጋት ቁርጠኛ መሆኑንም አስታውቋል። እርሱም ለመዋጋትና ለማዋጋት ተቆርጦ መነሳቱን ገልጿል። እንደርሱ ኹሉ የውጊያ ልምድ ያላቸው አዋጊዎችና ተዋጊዎች መኖራቸውንም ተናግሯል። ከጠላት ይልቅ አካባቢውን በሚገባ የምናውቀው ስለሆን ጠላትን ቀጥተን እናሸንፈዋለንም ብሏል። የአካባቢውን ሚሊሻና ወጣት አሰልጥኖ ወደ ውጊያ ይዞ መግባቱንም ተናግሯል።
በሀገር መከላከያ ሠራዊትና በአማራ ልዩ ኃይል ውስጥ ያገለገለውና አሁን ደግሞ በአማራ ሳይንት ሚሊሻ አደረጃጀት ውስጥ ጠላትን እየተፋለመ የሚገኘው ሳጅን ክንዱ ገድፍ ሚሊሻዎችን አሰልጥኖ ወደ ውጊያ መግባቱን ገልጿል።
❝የጠላትን ግፍ ለመጨረሻ ጊዜ ለማስቆም መከፈል የሚገባውን መስዋእትነት እንከፍላለን❞ ብሏል። ጠላትን በገባበት ገብተን እንቀብረዋለን ነው ያለው።
ጠላት በሚያናፍሰው ሐሰተኛ ወሬ ሕዝብ የሚያሸብሩ ሰዎችም እርምጃ ሊወሰድባቸው እንደሚገባ ነው የተናገረው።
የአማራ ሳይንት ወረዳ ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዋጋው ስሜነው የወረዳው ሚሊሻና አጠቃላይ የታጠቀ ኃይል ጠላትን በገባበት ለማስቀረት ወደ ግንባር መንቀሳቀሳቸውን ገልጸዋል።
የአማራ ሳይንት ወረዳ ሚሊሻ የሌሎች ወረዳዎች ሚሊሻዎችን በማደራጀት ወደ ግንባር እንዲዘምቱ ማድረጉንም አስታውቀዋል።
ሚሊሻው በአጭር ቀን ጠላትን መትቶ ሀገርንና ሕዝብን ነፃ ለማውጣት ቁርጠኛ መሆኑንም ገልጸዋል። በሚሊሻው አደረጃጀት ውስጥ በሀገር መከላከያ ሠራዊት ልምድ ያላቸው አዋጊዎችና ተዋጊዎች መኖራቸውንም ጠቁመዋል።
የአካባቢው ማኅበረሰብ በጠላት ውሸትና ፕሮፖጋንዳ እንደማይረበሽም ተናግረዋል።
የጠላትን ሐሰተኛ መረጃ በሚያሰራጩት ግለሰቦች ላይም እርምጃ እንደሚወስዱ ነው የገለፁት።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
ወራሪውን ጠላት ደምስስ!
የጀግንነት ታሪክህን ዳግም አድስ!
ያለ መስዋእትነት ድል አይገኝም!
ነፃነትህን አትስጥ!
ተዋርዶ ከመኖር በክብር መሞት ይሻላል!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ