አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፋጣኝ ውሳኔዎችን በመውሰድ ውጤታማ ግዳጅ ለመፈጸም ዕድል የሚሰጥ መሆኑን የቀድሞ የኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት ከፍተኛ መኮንኖች ተናገሩ።

142
ባሕር ዳር: ሕዳር 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) መንግሥት ያወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፋጣኝ ውሳኔዎችን በመውሰድ ውጤታማ ግዳጅ ለመፈጸም ዕድል እንደሚሠጥ ኢዜአ ያነጋገራቸው የቀድሞ የኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት ከፍተኛ መኮንኖች ተናግረዋል። የቀድሞው ገነት ጦር ትምህርት ቤት ምሩቃኑ ብርጋዴር ጄኔራል ሰብስቤ ንጋቱ እና ኮሎኔል ገበየሁ አበበ በቀድሞ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የጦር መኮንኖች ናቸው።
መኮንኖቹ በምሥራቅ ኢትዮጵያ የሶማሊያ ወረራ ብሎም በሰሜን ኢትዮጵያ የግዛት አንድነት የማስጠበቅ ተጋድሎ ውጤታማ ግዳጆች የፈጸሙና ሀገራቸውን በተለያዩ ኀላፊነቶች ያገለገሉ የሀገር ባለውለታዎች ናቸው። በየዘመኑ ከጠላት ጋር ይወግኑ የነበሩ ከሃዲዎች ነበሩ ያሉት መኮንኖቹ ጥቅምት 24/ 2013 ዓ.ም አሸባሪው ትህነግ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሰሜን እዝ ላይ የተፈጸመው ጭካኔ ግን በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም አያውቅም ብለዋል።
አስተያየት ሰጪዎቹ ድርጊቱ ወደር የማይገኝለት የከሃዲዎች የአረመኔነት መገለጫ ሲሉ ገልጸውታል፡፡
ኢትዮጵያውያን ከሃዲዎችን ግንባር ድረስ ከመዋጋት በተጨማሪ ሰርገው በመግባት የአሸባሪውን ተልዕኮ የሚያስፈፅሙ ተላላኪዎችን ተደራጅተው መመከት እንዳለባቸውም አሳስበዋል። ኢትዮጵያን ለማፍረስ በግልጽ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይል ለትግራይም ሆነ ለማንኛውም ሕዝብ የማይጠቅም ከሃዲ ቡድን መሆኑንም ከፍተኛ መኮንኖቹ ጠቅሰዋል።
በቅርቡ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኢትዮጵያ ያጋጠማትን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ወሳኝ እንደሆነም አብራርተዋል። በአዋጁ ከጥፋት ቡድኑ ጋር በግልጽና በስውር የሚሠሩ ባንዳዎችን እየመረመረ እርምጃ የሚወሰድበት ዕድል የሚሰጥ በመሆኑ አፋጣኝ ውሳኔዎችን በማራመድ ግዳጁን ለማፋጠን እንደሚያስችለው ተናግረዋል።
ወራሪውን ጠላት ደምስስ!
የጀግንነት ታሪክህን ዳግም አድስ!
ነፃነትህን አትስጥ!
ተዋርዶ ከመኖር በክብር መሞት ይሻላል!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአፋር ግንባር ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው ሰንጋዎችን ድጋፍ አደረገ፡፡
Next articleበባቲ በኩል ሚሌን ለመያዝ የሞከረው አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል በተባበረ ክንድ እየተደመሰሰ ነው