
ባሕር ዳር: ሕዳር 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በየደረጃው ያሉ የሥራ ኀላፊዎች በየግንባሩ ተሰልፈው የመሪነት ሚናቸውን መወጣታቸው ለሠራዊቱ ግዳጅ አፈጻጸም ትልቅ መነሳሳት መፍጠሩን በጋይንት ጋሸና ግንባር የተሰማራው መከላከያ ሠራዊት ገልጿል፡፡
የአማራ ሕዝብን አዋርዶ ሀገርን ለመበተን የተነሳው ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይል ዳግም አንገቱን እንዳያቃና አድርጎ ለመቅበር ሕዝቡ ልጆቹን መርቆ ወደ ግንባር እየሸኘ ነው፡፡ ጥሪቱን አሟጥጦ ለህልውና ትግሉ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እያደረገም ይገኛል፡፡ የህልውና ዘመቻውን ሕዝባዊ ማዕበል በላቀ ጥበብ ማስተባበር ደግሞ የሥራ ኀላፊዎች የቤት ሥራ ሆኗል፡፡ የክልል፣ የዞን እና የወረዳ የፖለቲካ መሪዎች እና የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ከፊት ተሰልፈው የህልውና ዘመቻውን እየመሩ ይገኛሉ፡፡
በአማራ ክልል ኮማንድ ፖስት የጋይንት ጋሸና ግንባር አስተባባሪው ሲሳይ ዳምጤ ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይልን ለመደምሰስ ከፌዴራል የፀጥታ መዋቅር ጋር የጋራ ዕቅድ ተዘጋጅቶ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡ በግንባሩ የተሰለፈው የፀጥታ ኀይል በተደራጀ አግባብ በሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይል ላይ ኪሳራ እያደረሰ ነው፡፡ የግልና የመንግሥት ታጣቂ ኃይልም በአንድ እዝ ተካትቷል፡፡
አቶ ሲሳይ እንዳሉት ሕዝቡ ጠላትን ለማጥፋት በከፍተኛ ደረጃ ወደ ግንባር በመትመም በጀግንነት እየተፋለመ ይገኛል፡፡ የህልውና አደጋውን ቀልብሶ ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይልን ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋት በሚደረገው እንቅስቃሴ የሥራ ኀላፊዎች ግንባር ቀደም ተሳታፊ መኾናቸውንም ጠቅሰዋል፡፡ ይህም የህልውና ዘመቻው ስምሪት ከበፊቱ የተሻለ እንዲሆን አድርጎታል ነው ያሉት፡፡


ዘጋቢ፡- ደጀኔ በቀለ-ከጋይንት -ጋሸና ግንባር
ወራሪውን ጠላት ደምስስ!
የጀግንነት ታሪክህን ዳግም አድስ!
ነፃነትህን አትስጥ!
ተዋርዶ ከመኖር በክብር መሞት ይሻላል!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ