ሸዋ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይልን ፍም ሆኖ እየለበለበው ነው

363
ባሕር ዳር: ሕዳር 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል ወደ ሰሜን ሸዋ ምድር ዘልቆ የመግባት ህልሙ እንደጉም እየበነነ ነው። የክልሉን መንግሥት የክተት ጥሪ ተቀብለው ወደ ግንባር ከዘመቱት የአማራ ሕዝባዊ ሠራዊት መካከል የኤፍራታና ግድም ወረዳ እና የአጣዬ ሚሊሺያዎች ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በመሆን ከፍተኛ ጀብዱ እየፈፀሙ ነው።
ወጣት ሃብታሙ ሲሳይ የክተት ጥሪውን ተቀብሎ ዘመቻውን ከተቀላቀሉት የሸዋ ሕዝባዊ ሠራዊት አባላት መካከል አንዱ ነው፡፡ ጠላት እንደገባበት መውጫው ቀላል አልሆነለትም ያለው ወጣት ሃብታሙ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል ላይመለስ ይቀበራል ነው ያለው።
ሁሉም የአካባቢው ማኅበረሰብና መልክዓ ምድሩ ሳይቀር ጠላትን እሾህ ሆኖ ነው የጠበቀው ያሉን ደግሞ ሌላኛው ዘማች ሽዋይልማ ተፈራ ናቸው፡፡ ወደ አማራ ምድር የገባ አንድም ጠላት ተመልሶ አይወጣም ባለበት ይቀበራል ብለዋል። ሸዋ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይልን ፍም ሆኖ እየፈጀው መሆኑን በመግለጽ፡፡
የአጣዬ ከተማ ከንቲባ አገኘሁ መክቴ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል በተደጋጋሚ ወደ ከተማዋ ለመግባት ጥረት አድርጎ እንደነበር ጠቁመው ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበታል ብለዋል፡፡ የሸኔ ሽብር ቡድን አቅምን የሸዋ አካባቢ ሕዝብ በሚገባ ያውቀዋል ያሉት ከንቲባው በመጣበት ይቀበራል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የሰሜን ሽዋ ዞን ብልጽግና ጽሕፈት ቤት ኅላፊ ካሳሁን እምቢአለ “የሸዋ ሕዝብ እንኳን ደጁ ድረስ የመጣን ርቆ ሄዶም እንዴት ጠላቱን መቅጣት እንዳለበት ጠንቅቆ ያዉቃል” ብለዋል፡፡ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል መጠነ ሰፊ ወረራ ለመፈፀም አቅዶ ቢመጣም በጀግናዉ መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ፣ ፋኖና ሕዝባዊ ሠራዊት አቀጡ ቅጣት እየተቀጣ ነው ብለዋል፡፡
ኅብረተሰቡ እያደረገ ያለዉ ተሳትፎ የሚደነቅ ነዉ ያሉት አቶ ካሳሁን ደጀንነቱ እስከ ጦር ግምባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ ጠላት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እስኪወገድ ድረስም የጋራ ርብርቡ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ኤሊያስ ፈጠነ
ወራሪውን ጠላት ደምስስ!
የጀግንነት ታሪክህን ዳግም አድስ!
ነፃነትህን አትስጥ!
ተዋርዶ ከመኖር በክብር መሞት ይሻላል!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“ከአማራ አብራክ የወጣችሁ ደም መላሾች የውትድርና ሳይንስን በመላበስ አማራ ከገጠመው የሕልውና አደጋ እንደምታወጡ አልጠራጠርም” ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ
Next articleለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት የአሜሪካ መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር በመከባበርና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ ሊሠራ ይገባል።