“ከአማራ አብራክ የወጣችሁ ደም መላሾች የውትድርና ሳይንስን በመላበስ አማራ ከገጠመው የሕልውና አደጋ እንደምታወጡ አልጠራጠርም” ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ

175
ሁመራ፡ ሕዳር 04/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሌጅ በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን የባእከር ጊዜያዊ የፖሊስ ማሰልጠኛ ለ9ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን የአማራ ልዩ ኀይል አባላት አስመርቋል።
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶክተር) እንዳሉት አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል በአማራና በአፋር ክልሎች ወረራ በመፈጸም ንጹሐንን እየገደለ፣ እየደፈረ፣ እያፈናቀለና እየዘረፈ ነው፡፡ ጠላት እያደረሰ ያለው ሰቆቃ የአማራ ሕዝብ ‘ሆ’ ብሎ እንዲነሳ አድርጎታል ብለዋል።
“የዛሬ የልዩ ኀይል ተመራቂዎች የአማራ ሕዝብ ለሕልውናው የማይደራደር መኾኑን ማሳያ ትኾናላችሁ ብለን እናምናለን” ነው ያሉት ዶክተር ይልቃል፡፡
ተመራቂ የልዩ ኀይል አባላት ባገኙት የወታደራዊ ሳይንስ ስልጠና ማንኛውንም ችግር በመቋቋም፣ በዓላማ በመጽናት ጠላትን መደምሰስ እንደሚጠብቅባቸው ነው ዶክተር ይልቃል ያሳሰቡት።
ርእሰ መሥተዳድሩ “ከአማራ አብራክ የወጣችሁ ደም መላሾች የውትድርና ሳይንስን በመላበስ አማራ ከገጠመው የህልውና አደጋ እንደምታወጡ አልጠራጠርም” ብለዋል።
የሚደረገው ትግል የመኖርና ያለመኖር ስለኾነ ብቸኛው መፍትሔ አሸባሪውን ኃይል ማጥፋት ብቻ ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ከሕዝብ የተሠጣቸውን አደራ ለተመራቂ የልዩ ኀይል አባላት ማስተላለፋቸውን ተናግረዋል፡፡
አሸባሪውን እና ወራሪውን የትግራይ ኀይል በያዛችሁት ትጥቅ በልበ ሙሉነት፣ በጀግንነት እና በወኔ በመደምሰስ ለአማራ ሕዝብ የድል ብስራት እንደሚያሰሙ ጥርጥር እንደሌላቸው ገልጸዋል፡፡
ዶክተር ይልቃል እንዳሉት የአማራ ሕዝብ በጠላት እየተጎሳቆለ፣ እየተገደለ፣ እየተደፈረና እየተዘረፈ በመኾኑ ጠላትን ለማጥፋት ጊዜ መውሰድ እንደማያስፈልግ ተናግረዋል።
ተመራቂ የልዩ ኀይል አባላት በጽናት አስፈላጊውን ኹሉ መስዋእትነት በመክፈል እንደ አባቶቻቸው ኹሉ ጠላትን በመቅበር በታሪክ ሊመዘገቡ እንደሚገባ ገልጸዋል።
በጽናት፣ በወኔ፣ በአንድነት እና በጀግንነት መንፈስ ጠላትን በአማራ ምድር መቀበር አለበት ብለዋል። ለዚህም መንግሥት በሚችለው አቅም ኹሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ አመላክተዋል።
ተመራቂዎች በዓላማ ጸንተው ከወገን ኃይል ጎን በመሰለፍ በሚደረገው አውደ ውጊያ ድል በማድረግ የአማራንና የኢትዮጵያን ሕዝብ ታሪክ ማደስ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ- ከሑመራ ባእከር
ወራሪውን ጠላት ደምስስ!
የጀግንነት ታሪክህን ዳግም አድስ!
ነፃነትህን አትስጥ!
ተዋርዶ ከመኖር በክብር መሞት ይሻላል!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article❝ወቅቱ አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያውያን በጋራ የምናጠፋበት ነው❞ አርቲስት እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነ
Next articleሸዋ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይልን ፍም ሆኖ እየለበለበው ነው