
ሕዳር 04/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአፋር ክልል የፈንቲረሱ ዞን ወጣቶች በፈጠሩት ጠንካራ አደረጃጀት አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይልን ታጣቂዎች መግቢያ መውጫ አሳጥቷቸዋል።
አካባቢያቸውን ተደራጅተው የሚጠብቁት ወጣቶች እንዳሉት፤ አሸባሪው ህወሓት በ27 ዓመት የስልጣን ዘመኑ የአፋርን ሕዝብ የሀብት ማካበቻ መሳሪያ አድርጎ ተጠቅሞበታል።
“ኢትዮጵያዊነትን ከአፋር ልብ ፍቆ ማውጣት ባይችልም ባይተዋር አድርጎት ቆይቷል” ብለዋል።
ወጣት መሐመድ አብዱ “ክህደት የማይሰለቸውን የሽብር ኃይል ለመደምሰስ ቀን ከሌሊት ነቅተን እየጠበቅን ነው” ብሏል።
አሸባሪው ህወሓት በአገዛዝ ዘመኑ የአፋርን የኢትዮጵያዊነት ሥነ ልቦና ለመሸርሸር መሥራቱን አስታውሷል።
የአፋር ሕዝብ ትምህርት እንዳይማር ሲያደርግ የነበረውን አሸባሪ ኃይል ለመቅበር ወጣቶች መዘጋጀታቸውን አረጋግጧል።

“አሸባሪ ኃይሉ ከገባበት ቦታ እንዳይወጣ ተደርጎ መቀበር አለበት” ብሏል።
“አፋር በሀገሩ ድርድር አያውቅም” የሚሉት ወጣቶቹ፤ “ይሄን ሀገርን ሊደፍር የመጣን ነውረኛ ኃይል በገባበት መቅበር ይገባል” ብለዋል።
በአፋር ክልል የፈንቲረሱ ዞን ብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ኃላፊ አቶ መሐመድ የሴጌሌ ጠላት በገባባቸው የአፋር ክልል አካባቢዎች መውጫ አጥቶ እየተቀጠቀጠ መሆኑን ገልጸዋል።
የሽብር ኃይሉን ለመደምሰስ ክልሉ በሚያደርገው ብርቱ ተጋድሎ የፌዴራል መንግሥትና የአማራ ክልል ለሚያደርጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ዶክተር ዓለሙ ስሜ “ለሀገር ክብርና ሉዓላዊነት መቆምን ከአፋር ሕዝብ ታላቅ ገድል መማር አለብን” ብለዋል።
“የሽብርኃይሉ በአፋር በኩል የጂቡቲን መስመር ለመዝጋት ያደረገው ተደጋጋሚ ሙከራ በእንቁዎቹ የአፋር ልጆች መክኖበታል፣ ፍላጎቱም ቅዠት ሆኖ ቀርቶበታል” ነው ያሉት።

አሸባሪው ኃይል ከተቀበረበት ጎሬ በወጣ ቁጥር ሞቱን እያፋጠነ መሆኑን የገለጹት ዶክተር ዓለሙ፤ በአፋርና አማራ ክልሎች የሽብር ኃይሉ የደረሰበት ኪሳራ ጥሩ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰዋል።
“ኢትዮጵያውያን ያሳየነው ትብብር አሸባሪዎቹን ህወሓትና ሸኔን ብቻ ሳይሆን የእኛን መሪ መሾም መሻር የሚፈልጉ የሩቅ ጠላቶችም ከነኩን የማንመለስ የእሳት አሎሎ መሆናችን ማሳያ ነው” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
