በባሕር ዳር ከተማ ግሸ አባይ ክፍለ ከተማ በአንድ ግለሰብ ቤት ከ3 ሺህ በላይ ጥይትና ሌሎች የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

516
ባሕር ዳር፡ ሕዳር 04/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የ2ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ በከተማ አስተዳደሩ ግሽ አባይ ክፍለ ከተማ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ተከማችቶ የተገኘ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል፡፡
የ2ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ ኀላፊ ምክትል ኮማንደር ጌትነት አበበ እንደገለጹት ጥቆማው የደረሰው ከማኅበረሰቡ ነው፡፡ በጥቆማው መሰረት ተጠርጣሪው ቤት ተከራይቶ ከሚኖርበት ቤት ፍተሻ በማካሄድ በግለሰቡ መኖሪያ ውስጥ ሁለት ክላሽ፣ ከ3 ሺህ በላይ የክላሽ እና የብሬን ጥይት፣ አንድ ኤፍዋን ቦንብ እና አንድ ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ በቁጥጥር መዋሉን ለአሚኮ ተናግረዋል፡፡
ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተካሄደ እንደሆነም ምክትል ኮማንደሩ አስረድተዋል፡፡
የቤት አከራዮች የተከራዮቻቸውን ማንነት በአግባቡ በማጣራት አድራሻቸውን ለፖሊስ እንዲያሳውቁም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በተለያዩ ሕገወጥ ተግባራት ላይ ተሰማርተው በሚገኙ አካት ላይ ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ ፖሊስ ከፍትሕ አካላት ጋር በቅንጅት እየሠራ እንደሚገኝም ምክትል ኮማንደር ጌትነት ጠቁመዋል፡፡
የክፍለ ከተማው ነዋሪ በተለይም ወጣቱ ለወቅታዊ ጉዳይ ትኩረት በመስጠት ከጸጥታ ኃይሉ ጋር እያደረጉት ያለው የቅንጅት ሥራ የሚበረታታ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ በቀጣይም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ደጀን አምባቸው
አካባቢዎን በንቃት ይጠብቁ!
ለጸጥታ ስጋት የሆኑ ጉዳዮችን ሲመለከቱ ለጸጥታ ኃይሎች ያሳውቁ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“በአማራ ክልል አሸባሪው የትግራይ ኃይል በወረራቸው አካባቢዎች ሕዝባዊ ሠራዊቱ ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በመቀናጀት እርምጃ እየወሰዱ ነው” የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ
Next article“አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል የጂቡቲን መስመር ለመዝጋት ያደረገው ሙከራ በአፋር ልጆች ተጋድሎ ቅዠት ኾኖ ቀርቶበታል” ዶክተር ዓለሙ ስሜ