“በአማራ ክልል አሸባሪው የትግራይ ኃይል በወረራቸው አካባቢዎች ሕዝባዊ ሠራዊቱ ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በመቀናጀት እርምጃ እየወሰዱ ነው” የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ

571
አዲስ አበባ: ሕዳር 04/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸውም በአማራ ክልል በአሸባሪው የትግራይ ኃይል በተወረሩ አካባቢዎች ሕዝባዊ ሠራዊቱ ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በመቀናጀት እርምጃ እየተወሰደ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል ከሽብርተኛው ሸኔ ጋር ጥምረት በመፍጠር ያደረገው እንቅስቃሴ በወገን ጦር የማጥቃት እርምጃ ኪሳራ ደርሶበታል፤ በከሚሴ የገባውን ጠላት የወገን ጦር ከበባ ውስጥ አስገብቶ እያጠቃ ነው ብለዋል።
በሌላ በኩል በአፋር ግንባር የወገን ጦር በወሰደው እርምጃ በጠላት ላይ እጅግ ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበታል ነው ያሉት።
በኦሮሚያ ክልል በአሸባሪው ሸኔ ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉንም ገልጸዋል፡፡
ለአሸባሪ ኃይሉ የስንቅና ትጥቅ ድጋፍ የሚያደርጉትን በመለየትም ደጀን አልባ እንዲሆን እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።
በዘመቻው ሕዝቡ እያሳየ ላለው አንድነትና ደጀንነት ምስጋና ይገባዋል ብለዋል፡፡
መንግስት ባደረገው ጥሪ መሰረት በርካታ ወጣቶች በተለያዩ አደረጃጀቶች በመግባት እየተመዘገቡ ይገኛሉ ያሉት ዶክተር ለገሰ ይህም ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚኖርበት ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡- እንዳልካቸው አባቡ- ከአዲስ አበባ
ወራሪውን ጠላት ደምስስ!
የጀግንነት ታሪክህን ዳግም አድስ!
ነፃነትህን አትስጥ!
ተዋርዶ ከመኖር በክብር መሞት ይሻላል!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየሕዝባዊ ሠራዊት አባላት ለአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ኃይል የእግር እሳት መሆናቸውን በተግባር እያሳዩ ነው፡፡
Next articleበባሕር ዳር ከተማ ግሸ አባይ ክፍለ ከተማ በአንድ ግለሰብ ቤት ከ3 ሺህ በላይ ጥይትና ሌሎች የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡