
ሕዳር 04/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ የዩጋንዳ አምባሳደር ኾነው አገልግለዋል፡፡ ኢትዮጵያን እና የኢትዮጵያን እውነትም ለይተው ያውቃሉ፤ የቀድሞ በኢትዮጵያ የዩጋንዳ አምባሳዳር ኤዲዝ ሴምፓላ፡፡ እናም ይላሉ አምባሳደር ኤዲዝ ሴምፓላ በኢትዮጵያ የነበራቸው ቆይታ የሀገሪቱን ወቅታዊ ችግሮች ለይተው እንዲያውቁ ረድቷቸዋል፡፡
ሕወሓት ተመልሶ ወደ ስልጣን መምጣት ይፈልጋል የሚሉት አምባሳደር ኤዲዝ ሴምፓላ “የኢትዮጵያ ወቅታዊ ችግር ምንጩ ሕወሓት ነው፤ ምክንያቱ ደግሞ ስልጣን በቃኝ የማይል፣ ሴረኛ እና ጨካኝ በመሆኑ ነው” ይላሉ፡፡
በሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) መሪነት ኢትዮጵያ ከጎረቤት ኤርትራ ጋር ለሁለት አስርት ዓመታት የዘለቀን ቁርሾ መፍታት፣ ልዩነትን በይቅርታ ማጥበብ እና በዲሞክራሲያዊ መንገድ ምርጫ ማድረግ ስኬቶች እንደነበሩም አውስተዋል፡፡
አፍሪካዊያን ጋዜጠኞች የአንዳንድ ምዕራባዊያንን የቅኝ ግዛት ዘመን አስተሳሰብን ከማራገብ ወጥተው የአህጉሪቷን ችግሮች ነቅሰው በማውጣት የመፍትሔው አካል መሆን አለባቸው ብለዋል፡፡
ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ጥያቄ የተነሳላቸው አምባሳደር ኤዲዝ ሴምፓላ ግብጽ ከመጠን ባለፈ ራስ ወዳድነት ውኃውን ብቻዋን ለመጠቀም የምታራምደው አስተሳሰብ የተፋሰሱን ሀገራት ተፈጥሯዊ መብት የሚጋፋ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የተፋሰሱ ሀገራት ተፈጥሮ የሰጠቻቸውን ጸጋ በትብብር ከመጠቀም የተሻለ አማራጭ የላቸውም ነው ያሉት፡፡
በታዘብ አራጋው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
