
ሕዳር 04/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአርጡማ ፉርሲና የኤፍራታና ግድም ሰንሰለታማ ተራራዎች ሰሞኑን ጠላት እንደ ቅጠል ሲረግፍባቸው ሰንብቷል። በለስ ቀንቶት እጁን ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የሰጠው የወራሪውና ሽብርተኛው የትግራይ ኃይል ህይወቱን ሲያተርፍ በጦር ግንባር ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶበታል።
ጠላትን መመከት ሳይሆን ጠላትን ባለበት ቦታ ቀጥቅጦ የመቅበር ሥራ በቀጣናው በታላቅ ጀብዱ እየተከናወነ ይገኛል።
በግንባሩ አዛዥ ከሆኑት አንዱ ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ ረጋሳ በቀጣናው የተሰማራው መከላከያ ሠራዊት የጠላትን ሀገር የማፍረስ ህልም እያከሸፈ ከፍተኛ ድል እየተቀዳጀ መሆኑን ተናግረዋል።
አሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ኃይል ያሰማራው ኃይል ባለበት እየተቀበረ ነው ያሉት ብርጋዴር ጀነራሉ የቡድኑ አባላት ሙት፣ ቁስለኛና ምርኮኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የአካባቢው ማኅበረሰብ ብሎም መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እያሳዬ ያለው የደጀንነት ተግባር እጅግ አበረታች ነው ብለዋል።
አሸባሪውን ኃይል ለማስወገድ አሁንም የተጠናከረ ርብርብ ያስፈልጋል ያሉት ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ የጠላትን መውጫና መግቢያ ቦታዎችን እየተከታተለ ለሠራዊቱ ጥቆማ እንዲሰጥም አሳስበዋል።
ዘጋቢ:- ኤልያስ ፈጠነ
ወራሪውን ጠላት ደምስስ!
የጀግንነት ታሪክህን ዳግም አድስ!
ነፃነትህን አትስጥ!
ተዋርዶ ከመኖር በክብር መሞት ይሻላል!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
