ሮይተርስ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ ሐሰተኛ መረጃን እያሰራጨ ነው፡፡

132
ሕዳር 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ሮይተርስ በኢትዮጵያ የጸደቀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዜጎች የብሔር ማንነታቸውን የሚያመላክት መታወቂያ እንዲይዙ ያስገድዳል በሚል የሐሰት ዜና እያሰራጨ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ።
መረጃ ማጣሪያው የሮይተርስ ዘገባ ከእውነት የራቀ እና በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተቀመጡ መመሪያዎች ውጭ መሆኑንም ገልጿል።
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዜጎች የብሔርን ማንነት የማያመላክቱና ከመታወቂያ ተመጣጣኝ የሆኑ እንደ መንጃ ፈቃድ፣ የሥራ ቦታ መታወቂያ እና ፓስፖርትን እንዲጠቀሙ እንደሚፈቅድም አመላክቷል።
ሮይተርስ የብሔር ማንነትን የሚገልጽ መታወቂያ መያዝ ግዴታ ነው ተብሎ መዘገቡ የተሳሳተ መሆኑንም ነው የመረጃ ማጣሪያው የገለጸው።
ወራሪውን ጠላት ደምስስ!
የጀግንነት ታሪክህን ዳግም አድስ!
ነፃነትህን አትስጥ!
ተዋርዶ ከመኖር በክብር መሞት ይሻላል!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article❝እንዲህ ወደ አማራ ግፋፎ አትጣሉበት፣ ረመጡ አይለቅም ጀግኖቹ ያሉበት❞
Next articleየምሥራቅ እና የምዕራብ በለሳ አናብስት በዋግኽምራ ግንባር ታላቅ ጀብድ እየፈጸሙ ነው።