
ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይልን ለመደምሰስ የተቀናጀ ዘመቻ እያካሄደ መሆኑን የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አስታወቀ፡፡
ሕዳር 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ወረራ ማካሄድ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ንጹሐንን ገድሏል፤ ሴቶችን ደፍሯል፣ አፈናቅሏል፣ ሀብት ንብረት ዘርፏል፤ አውድሟል። ባደረገው መጠነ ሰፊ ወረራ ሕዝብ እንዲጎሳቆል እና ለርሃብ እንዲጋለጥ አድርጓል።
በደረሰበት በደል በቁጭት የተነሳው የዋግ ነዋሪ እና ከተለያዩ አካባቢዎች የተሰባሰበው ሕዝባዊ ሠራዊት ሽብርተኛውን የትግራይ ወራሪ ኃይል ለመደምሰስ እየተፋለመ መሆኑን የዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ምክትል አስተዳዳሪ ተስፋዬ ገብሬ ተናግረዋል።
ከቀያቸው የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ አካባቢያቸው በመመለስ ሕዝባዊ ማዕበሉን ተቀላቅሎ እልህ አስጨራሽ ፍልሚያ እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።
እየተካሄደ የሚገኘው ፍልሚያ በአመርቂ ውጤት እንዲደመደም ወደ ውጊያ መገባቱን አቶ ተስፋዬ ተናግረዋል ።
ምክትል አስተዳዳሪው እንደተናገሩት ሕዝባዊ ሠራዊቱ ከወገን ጦር ጋር በመሆን ጠላትን የመደምሰስ ሥራ ጀምሯል፤ ጠላት በሕዝባዊ ሠራዊት ከበባ ውስጥ ገብቷል፡፡ በአጭር ጊዜ አካባቢውን ነፃ እናደርጋለን ብለዋል አቶ ተስፋዬ።
ኹሉም የዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር የሥራ ኀላፊዎች ሕዝባዊ ሠራዊቱን በመምራት በግንባር ላይ እንደሚገኙ ነው ምክትል አስተዳዳሪው ያስታወቁት፡፡
እንደ ምክትል አስተዳዳሪው ገለጻ የብሔረሰብ አስተዳደሩ ሕዝብ ከዚህ በፊትም ሽብርተኛው የትግራይ ወረራ ኃይልን አንገት አስደፍቷል፤ በቀጣይም እስትንፋንሱን በመዝጋት የኢትዮጵያን አሸናፊነት በተግባር ያረጋግጣል፤ በቅርቡም የድል ብስራትን ይበሰራል።
ዘጋቢ፦ አዳሙ ሽባባው-ከዋግ ኽምራ ግንባር
ወራሪውን ጠላት ደምስስ!
የጀግንነት ታሪክህን ዳግም አድስ!
ነፃነትህን አትስጥ!
ተዋርዶ ከመኖር በክብር መሞት ይሻላል!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
            
		