ወደ ሸዋ ለመግባት የሞከረው አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል እየተቀጣ ነው።

458
ሕዳር 02/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ኃይል እና የሱ ተላላኪ የሆነው ኦነግ ሸኔ አማራን ለማጥፋትና ለመዝረፍ በማሰብ በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ወረዳዎች አድርጎ ወደ ሸዋ ቆላማ አካባቢዎች ለመግባት ተኩስ ቢከፍትም በደቡብ ወሎ፣ በከሚሴ፣ በሸዋ ጀግኖች ጥምር ኃይል፣ በመከላከያ ሠራዊት እና በአማራ ልዩ ኃይል እየተመታ እንደሚገኝ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የመረጃ ምንጮች ገልጸዋል።
ጠላት ወደ ሰሜን ሸዋ አካባቢዎች በተለይ ካራ ቆሬ እና ማጀቴ ሰርጎ ለመግባት ቢሞክርም በመከላከያ ሠራዊት፣ በአማራ ልዩ ኃይል እና ከተለያዩ ወረዳዎች ጦር ሰብቀው በተመሙ የሸዋ ፋኖ እና ሚሊሻ ከባድ ጥቃት ደርሶበታል፡፡ በማጀቴና አካባቢው በተደረገበት የተቀናጀ ጥቃት የተረፈው ጥቂት የአሸባሪው የትግራይ ወራሪ በመከበቡና ማምለጫ ቀዳዳ በማጣቱ በቤተ-እምነቶች በመጠለል ለማምለጥ እየጣረ ይገኛል፡፡
በተመሳሳይ ጠላት በደቡብ ወሎ ዞን አዋሳኝ ቀበሌዎች በአይበገሬዎቹ በከሚሴ፣ የደቡብ ወሎ አልቡኮና ቃሉ እንዲሁም የሸዋ ፋኖና ሚሊሻ ተመትቶ ተበታትኗል፡፡
በተመሳሳይ በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን በጅሌ ጥሙጋ እና አርጡማ ፉርሲ ወረዳዎች አንዳንድ ጸረ-ሕዝብ ኃይሎች ጉያ ተደብቀው ጥቃት ለማድረስ ቢሞክሩም በብሔረሰብ አስተዳደሩ እና በሰሜን ሸዋ ወረዳዎች በተሰለፉ ጥምር ተዋጊዎች ቅንጅት እንዲሁም በጀግናው የአማራ ልዩ ኃይልና የሀገር መከላከያ ሠራዊት ጥቃት የጠላት ኃይል መጠነ ሰፊ ኪሳራ ደርሶበታል፡፡
አሁንም በየእርሻና በጥሻ ተበታትኖ ከጥቃት ለማምለጥ የሚጥረውን ተስፋ ያጣ ጠላት እና ተላላኪውን በመልቀምና አካባቢውን ከወራሪው ኃይል ነጻ ለማድረግ ተጋድሎ እየተደረገ ይገኛል፡፡
በሌላ በኩል በሰሜን ወሎ ዞን የኮን ወረዳ ፋኖና ሚሊሻ በሥፍራው በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል በተወረሩ አካባቢዎች የሚገኙ ሚሊሻና ፋኖዎች የጠላትን ወታደራዊና የሎጅስቲክ መስመሮች ላይ ጥቃት በማድረስ ቁሳዊና ሰብዓዊ ኪሳራ እያደረሱበት መሆኑን ከምንጮቻችን የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article❝እርስ በርስ በመደማመጥና በመተባበር አካባቢያችንን በንቃት እየጠበቅን ነው❞ የሰንበቴ ከተማ ወጣቶች
Next articleሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይልን ለመደምሰስ የተቀናጀ ዘመቻ እያካሄደ መሆኑን የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አስታወቀ፡፡