❝እርስ በርስ በመደማመጥና በመተባበር አካባቢያችንን በንቃት እየጠበቅን ነው❞ የሰንበቴ ከተማ ወጣቶች

146
ሕዳር 02/2014 ዓ.ም (አሚኮ) እርስ በርስ በመደማመጥና በመተባበር አካባቢያቸውን በንቃት እየጠበቁ መሆኑን የሰንበቴ ከተማ ወጣቶች ገለጹ።
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል ሀገር ለማፍረስ የጀመረውን እኩይ ሴራ ኢትዮጵያውያን በተባበረ ክንዳቸው እየመከቱት ነው።
በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር የሰንበቴ ከተማ ወጣቶች እንደገለጹት፤ አካባቢያቸውን በመጠበቅ፣ መከላከያን በመደገፍና ወደ ግንባር በመዝመት ለጸጥታ ኃይሉ ደጀንና አጋርነታቸውን እያሳዩ ነው።
ወጣቶቹ ጠንካራ አደረጃጀት በመፍጠርና በመተባበር አካባቢያቸውን ነቅተው ከጠላት እየጠበቁ መሆኑንም ገልጸዋል።
ወጣቶቹ ለመከላከያና ለሌሎች የጸጥታ አካላት አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረጉ መሆኑንም እንዲሁ።
የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጀማል ዑመር ወጣቶች የአካባቢያቸውን ሰላም በማስጠበቅ ረገድ የማይተካ ሚና እያበረከቱ መሆኑን ገልጸዋል።
በተመሳሳይ የአካባቢው ማኅበረሰብ ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር በመቀናጀት ሰርጎ ገቦችንና የውስጥ ባንዳዎችን የመከላከል ሥራ እያከናወነ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሕመድ ሐሰን በበኩላቸው አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚያደርገውን ጉዞ ለመግታት ኅብረተሰቡ ተቀናጅቶ እየሠራ መሆኑን አስታውቀዋል።
የሽብር ኃይሉን በመከላከል ረገድ ጀብድ የፈጸሙ ጀግኖች መኖራቸውንም አመላክተዋል።
ለአብነትም አምስት የአካባቢው ወጣቶች በርካታ የሽብር ኃይል አባላትን በመደምሰስ በደማቅ የታሪክ ቀለም ተጽፎ የሚዘከር ጀብዱ መፈጸማቸውን እንደገለጹ ኢዜአ ዘግቧል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleዓለም አቀፍ ተቋማት እና ድርጅቶች የኢትዮጵያን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አክበረው መንቀሳቀስ አንደሚገባቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡
Next articleወደ ሸዋ ለመግባት የሞከረው አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል እየተቀጣ ነው።