የቆቦና የግዳን ፋኖና ሚሊሻዎች በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል ላይ እርምጃ መውሰዳቸውን ቀጥለዋል።

489
ሕዳር 01/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የቆቦ አካባቢና የግዳን ፋኖዎች ሕዝብን በማሰቃየት፣ በመግደልና በመዝረፍ ላይ በሚገኘው አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል የተቀናጀ ጥቃት በመፈፀም ላይ መሆናቸውን ከአካባቢው የአሚኮ የመረጃ ምንጮች ያደረሱን መረጃ ያመለክታል።
ፋኖዎቹ ሕዝብን በማስተባበር በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል የዘረፈውን ንብረት ወደ ትግራይ እንዳይወስድ፣ በወረራቸው አካባቢዎች እንዳይንቀሳቀስ ጥቃት በመፈፀም ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ አድርሰውበታል።
ከቆቦና አካባቢው ሀብትና ንብረት ጭኖ ለመውሰድ የመጣ ኃይል ላይ ጥቃት በማድረስ መኪናዎቹን አውድመው የቀሩትን ማርከዋል።
የዘራፊውን ኃይል ሲያስተባብር የነበረው የወራሪው ኃይል የመቀሌ ኮማንድ ፖስት የሎጅስቲክ ከፍተኛ አመራር ላይም እርምጃ ተወስዷል።
በተመሳሳይ የግዳን ወረዳ ፋኖና ሚሊሻዎች ሎጅስቲክ ጭኖ ሲንቀሳቀስ የነበረን ከአስር በላይ መኪና ጥቃት ፈጽመው ቀሪዎችን መማረካቸው ታውቋል።
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል በቆቦና አካባቢው እንዲሁም በግዳን የሕዝቡን ሰብል በመሰብሰብ ወደ ትግራይ ለመጫን የሚያደርገውን ጥረት ለማክሸፍ በፋኖዎችና ሚሊሻዎች አስተባባሪነት ሕዝቡ እየታገለው ይገኛል።
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል በየጊዜው የወረራ ስልት እየቀያየረ ሕዝብን በማሰቃየት ላይ ቢሆንም ፋኖዎችና የአካባቢው አርሶ አደር አሳቻ ሰዓትና ቦታ በመጠበቅ አሸባሪውን ኃይል መውጫና መግቢያ እያሳጡት እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኀይል በነፋስ መውጫ ሴቶችን በቡድን አስገድዶ መድፈሩን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አጋለጠ፡፡
Next article❝አምነስቲ ኢንተርናሽናል ያወጣው የሽብርተኛው የሕወሓት አረመኔያዊ ድርጊት የሰው ዘር ኹሉ ሊቃወመው የሚገባ ነው❞ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት