
ሕዳር 01/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አምነስቲ ኢንተርናሽናል ይፋ እንዳደረገው አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኀይል በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን ነፋስ መውጫ ከተማ በወረረበት ወቅት ሴቶችን በቡድን አስገድዶ ደፍሯል፡፡
በነፋስ መውጫ የሚኖሩ 16 ሴቶች በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኀይል ተገደው መደፈራቸውን ለድርጅቱ ይፋ አድርገዋል፡፡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል እንዳለው የሽብር ቡድኑ በአካባቢው ወረራ በፈጸመበት ወቅት አስገድዶ ከመድፈር ባለፈ ንብረት ዘርፏል፤ አካላዊ እና ስነ ልቦናዊ ጥቃት አድርሷል፡፡
በከተማዋ የሚገኙ የጤና ተቋማት መውደማቸውን እና መዘረፋቸውን ነው ተቋሙ የገለጸው፡፡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ካነጋገራቸው ከ16 ሴቶች ውስጥ 14ቱ በቡድን መደፈራቸውን ገልጸዋል ብሏል፡፡
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኀይል በነፋስ መውጫ ከተማ ወረራ በፈጸመበት ወቅት ከፍተኛ ጥፋት ማድረሱን ነው የገለጸው፡፡
አሸባሪ ኀይሉ በተመሳሳይ በሌሎች የአማራ እና አፋር ክልሎችም ጥቃት መሰንዘሩን አንስቷል፡፡
አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተደፈሩ ሴቶች ቁጥር 14 ናቸው ቢልም ከ70 በላይ ሴቶች በቡድን መደፈራቸውን የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል መግለጻቸው ታውቋል፡፡
የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ዋና ጸሐፊ አግነስ ካላማርድ ‹‹ ከተጎጅዎች አንደበት ያዳመጥነው የጉዳት መጠን `አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኀይልን´ በጦር እና በሰብዓዊነት ወጀል የሚያስጠይቀው ነው›› ብለዋል፡፡
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኀይል እየፈጸመው ካለው ማንኛውንም የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት በአስቸኳይ ሊታቀብ እንደሚገባም ዋና ጸሐፊው ጠይቀዋል፡፡
አሚኮ የትግራይ ወራሪ ኃይል የፈፀማቸውን ጥፋቶች በተደጋጋሚ ማጋለጡ ይታወሳል ።
በዳግማዊ ተሠራ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ