
የትግራይ ወራሪ ከፍጥረቱ ጀምሮ ፀረ-ዐማራ እና ፀረ-ኢትዮጵያ ኾኖ የተነሳ ድርጅት ነው፡፡ የዐማራን ሕዝብ እንደ ቀዳሚ ጠላት ፈርጆ መነሳቱ በታሪክ የተመዘገበ እውነታ ነው፡፡ ጥላቻውንም በፖለቲካ ዓላማ ማብራሪያው ማኒፌስቶ ላይ በግልፅ ያሰፈረ፣ በሐሰት ትርክት ለበቀል የተነሳ የጥላቻ መንጋ ነው፡፡ ሴረኝነት፣ ተስፋፊና ተገንጣይነት የዚህ ድርጅት መገለጫ ባህሪያት ናቸው፡፡
የትግራይ ወራሪ ገዳይ ነው፣ አፋኝ ነው፣ አሳዳጅ ነው፣ የግዛት ተስፋፊ ነው፣… ስንል ለሁሉም ድርጅታዊ ክፋቱ ከወልቃይት ጠገዴ ዐማራ በላይ የተሻለ አስረጅ ምሳሌ የለም፡፡ በዐማራ ደምና ሀብት ታላቋን ትግራይ የመመስረት እቅዱን ለማሳካት ሲል፤ ዐማራን ገድሏል፤ አኮላሽቷል፤ ሀብቱን ዘርፏል፤ መሬቱንም ወርሯል፡፡ ለዚህ ምስክር ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምትና ራያን መጥቀስ ይቻላል፡፡
አሁንም እየሆነ ያለው የዚሁ የጥፋት ታሪኩ አዙሪት አካል ነው፡፡ ካለፈው ሰኔ ወር ጀምሮ በመኾኒ፣ ቆቦ፣ አጋምሳ፣ ንፋስ መውጫ፣ ጭና፣ ውጫሌ፣ ኮምቦልቻ፣… የተፈፀመው የጅምላ ጭፍጨፋ፣ ወያኔ በዐማራ መቃብር ሀገረ-ትግራይን የመፍጠር ምኞቱ አካል ነው፡፡
የትግራይ ወራሪ አፓርታይዳዊ አገዛዝ ከተዘረጋ ጀምሮ በወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ታውጆ ተፈጻሚ ተደርጓል፡፡ ለዚህም የሰውና የጅምላ መቃብር ምስክሮችን አስረጅ ምሳሌ አድርገን እናቀርባለን፡፡ ከሁመራ ኤርፖርት ግቢ የጅምላ መቃብር እስከ ማይካድራው ጭፍጨፋ፤ በየዋሻውና የምድር ውስጥ እስር ቤቶች በጅምላ ያለቀው ወገናችን ስፍር ቁጥር የለውም፡፡
ባለፉት ሠላሳ ዓመታት ዓለም ጀሮ የነፈገው የዘር ማጥፋት ወንጀል በወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ሕዝብ ላይ ተፈጽሟል፡፡ ምናልባትም በብዙኃኑ ኢትዮጵያውያንና በተወሰኑ የዓለማቀፉ ማኅበረሰብ አባላት ዘንድ የተሰማው ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም. የሕግ ማስከበር ዘመቻው ከተጀመረ በኋላ ጥቅምት 30/2013 ዓ.ም. በማይካድራ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ብቻ ነው፡፡ የወልቃይት ጠገዴ ዐማራ ግን ባለፉት ሠላሳ ዓመታት በርካታ ማይካድራዎችን አይቷል፡፡ በየትኛውም የዓለም ክፍል የተፈጸሙ የዘር ማጥፋት ወንጀሎች አንዴ ተጀምረው በተወሰነ የጊዜ ገደብ የተጠናቀቁ ቢሆንም፣ ወልቃይት ጠገዴ ላይ የተፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ግን በአይነትም ኾነ በድርጊት የተለየ ነው፡፡ ለሠላሳ ዓመታት ያለማቋራጥ መዋቅራዊ በሆነ መንገድ ነባሩን ሕዝብ የማጥፋት ስራ ተሠርቷል፡፡ በዚህም ባለፉት ሠላሳ ዓመታት በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ዐማራዎች በማንነታቸው ተገድለዋል፡፡ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ወገኖቻችን ወደ መቀሌና ወዳልታወቁ ስፍራዎች ታፍነው ተወስደው በእስር ሲማቅቁ ኑረዋል፤ ብዙዎችም ባሉበት አልፈዋል፡፡
በሠላሳ ዓመቱ የወያኔ አፓርታይዳዊ ዘመን ከቆላ እስከ ደጋ አምስት መቶ ሺህ የሚደርስ የወልቃይት ጠገዴ ዐማራ ከርስቱ ተፈናቅሎ፣ ወደጎረቤት ሀገራትና ወደጎንደር አልፎም ወደ መሀል ሀገር እንዲሰደድ ተደርጓል፡፡
የትግራይ ወራሪ በግዛት ተስፋፊነቱ ተከዜን ሲሻገር በእብሪት መንፈስ የጥላቻ ንግግሩን እንዲህ ነበር ያንፀባረቀው፡- “ ካብ ወልቃይት ንህና ንደልዮ ደቂ አንስትዮምን መሬቶምን ጥራህ ዩ” (ትርጉም፡- “እኛ ከወልቃይት የምንፈልገው ሴቶቹን እና መሬቱን ነው”) ይህን በትግረኛ ቋንቋ የሚነገር ከኢትዮጵያዊ ጨዋነት የወጣ የጥላቻ ንግግር ገና ከመነሻው ሲናገረው ነበር፡፡ ይህ ንግግር አስቀድሞ የነበረ ከመሆኑ አኳያ፣ በሕግ ቋንቋ የዘር ማጥፋት የሐሳብ ክፍልን የሚያስረዳ የጥላቻ አባባል ነው፡፡ ከጥላቻ ማኒፌስቶው ጀምሮ መሰል የጥላቻ ንግግሮችን በማሳደግ የወልቃይት ጠገዴን ሕዝብ ላለፉት ሦስት አስርት ዓመታት በስውርና በግልፅ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲፈፅምበት ኑሯል። ማይካድራ አንዱ ማሳያ እንጂ፣ በዐማራ ላይ የተፈፀመ ብቸኛው የዘር ማጥፋት ወንጀል አይደለም፡፡
የማይካድራን ጭፍጨፋ ስናስብ ጭፍጨፋው የፀረ-ዐማራ ትርክት ውጤት ስለመሆኑ ልብ ልንለው ይገባል፡፡ ጥቅምት 30/2013 ዓ.ም በማይካድራ ከተማ የተፈፀመው የጅምላ ጭፍጨፋ በ1968 ዓ.ም ወያኔ ያዘጋጀው ዐማራን የማጥፋት ፍኖተ መርሁ አካል ነው።
የጅምላ ጭፍጨፋው የተፈፀመው ‹ሳምረ› የሚባለው የሰፋሪ ትግሬ ወጣቶች ቡድን ከትግራይ ወራሪ ልዩ ኃይል ፖሊስና ሚሊሻ ጋር በመሆን ነበር፡፡ አፈፃፀሙም በየጎዳናውና ከቤት ቤት በመዘዋወር አስቀድመው የለዩዋቸውን ወገኖቻችንን በከፍተኛ ግፍና ጭካኔ በዱላ በመደብደብ፣ በጩቤ በመውጋት፣ በገጀራና በፈራድ (ወይም ፋስ መጥረቢያ) በመምታት፣ በገመድ በማነቅና በጥይት ተኩሶ በመምታት በጅምላ ጨፍጭፈዋቸዋል፡፡ በዚህ የጅምላ ጭፍጨፋ የወልቃይት ጠገዴ ዐማራን መሬት በመውረር ሀብት ንብረት ያፈሩ የትግራይ ባለሃብቶች በአካል፣ በሐሳብና በገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
ጥቅምት 30/2013 የጅምላ ጭፍጨፋው ከመጀመሩ ቀደም ብሎ፣ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፃሚዎቹ የትግራይ ተወላጅ የሆኑና ዐማራ የኾኑትን ለመለየት መታወቂያ ካርድ እየተመለከቱ ማጣራት አድርገዋል። የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ሴቶች እና ሕጻናት ጥቃቱ ከመጀመሩ በፊት አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ተነግሯቸው ሊወጡ ችለዋል። ጭፍጨፋው ሲጀመር በልዩ ሁኔታ የዐማራ ብሔር ተወላጆች በብዛት በሚኖሩበት ልዩ ስሙ ‹‹ግንብ ሠፈር›› በሚባለው መንደር እስከወልቃይት ቦሌ ሠፈር ድረስ የሚገኙ ወገኖቻችን፣ ግፍና ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ተገድለዋል።
ጭፍጨፋው የተጀመረው ዓብይ ፀጋዬ የተባለን ዐማራ ከቤቱ ፊት ለፊት በጥይት በመግደል፣ ቤቱንና አስከሬኑን በእሳት በማቃጠል ነው። በሰማዕቱ ዓብይ ፀጋዬ የተጀመረው ጭፍጨፋ እስከ ለሊቱ 9:00 ድረስ በወገኖቻችን ላይ አሰቃቂ የጅምላ ጭፍጨፋው ተጠናክሮ በመቀጠሉ 1 ሺህ 644 ዐማራዎች የጉዳት ሰለባ ሁነዋል። የተጨፈጨፉ 1 ሺህ 563 ሲሆኑ፤ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ደግሞ 81 ናቸው፡፡ በዚህ ጭፍጨፋ የተነሳ በርካታ ሕጻናት ያለ ወላጅ ቀርተዋል።
የማይካድራ የዘር ማጥፋት ድርጊት ፈፃሚዎች የዘር ማጥፋት ድርጊቱን የፈፅሙት በጀኔቫ ቃልኪዳን አንቀፅ ቁጥር 2 እና በሮም ድንጋጌ አንቀፅ ቁጥር 6 እና 7 ከዘር ማጥፋት ወንጀል ጥበቃ የሚደረግለት አንድ የሆነን የብሔር፣ የዘር… ቡድን የሆነውን (የወልቃይት ዐማራ) ዘር በመላ ወይም በከፊል ለማጥፋት በማሰብ ነው፡፡
በመሆኑም
1) የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ዐቃቤ ሕግ፣ የማይካድራ የዘር ማጥፋት ወንጀል መርምሮ የወንጀል ድርጊት ፈፃሚዎቹ ላይ ክስ በመስረት ለማይካድራ ሰለባዎች ዓለም አቀፍ ፍትሕ እንዲሰጥ እንጠይቃለን፡፡
2) የፌዴራል መንግሥት የወልቃይት ሕዝብ ለዘር ማጥፋት ወንጀል የተዳረገው የማንነት ጥያቄ በማንሳቱ ምክንያት ስለሆነ በሕግና በሥርዓት ላቀረበው ጥያቄው ምላሽ በመስጠት ሕጋዊ መልክ እንዲያሲዝ በሰማዕታት ስም እንጠይቃለን፡፡
3) የወልቃይት ዐማራ ለደረሰበት ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ሥነ-ልቦናዊ ጉዳት እና ለተፈፅመበት የዘር ማጥፋት ወንጀል በደረሰው ጉዳት እና በተፈፀመው ጥፋት ልክ ካሳ እንዲከፈል እንጠይቃለን፡፡
4) የትግራይ ወራሪ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአካባቢው ሀገራት የደኅንነት ስጋት ስለመሆኑ በተጨባጭ የተረጋገጠ በመሆኑ፣ እርሱ ከሚመራው መንጋ ጋር ከነ አስተሳሰቡ በሕዝባዊ ትግል ወደመቃብር እንዲወርድ፣ የህልውናና ሀገር የማዳን ተጋድሎው ተጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩላችንን ጥሪ እናቀርባለን፡፡
በመጨረሻም
‹ማንነታችን ዐማራ፤ ድንበራችን ተከዜ ነው!› በሚል ለቃላቸው ታምነው ሰማዕት የሆኑ የወገኖቻችንን ዓላማ ከግብ ሳናደርስ የሚዘል ክንድም ኾነ ሸብረክ የሚል ጉልበት እንደማይኖረን በተግባር ማረጋገጣችንን እንቀጥላለን፡፡ ተከዜ በትላንት፣ በዛሬና በነገ ሰማዕታት የሚጸና የዐማራ ወሰን ነው!! የህልውና ትግላችን በዘላቂና አስተማማኝ ድል በመቋጨት የሰማዕታቱን አደራ እንወጣለን!!
እንደሀገር፤ ነፃ ሕዝብ እንደነበርነው ነፃ ሕዝብ ሁነን የጋራ ኢትዮጵያን በወንድማማችነት ስሜት እንገነባለን፡፡ ለመጭው ትውልድ ነፃነት ዛሬ ለመሰዋት ዝግጁ ነን፡፡ ይህ ትውልድ በወያኔ ቀንበር ስር በዳግም ባርነት ከሚያልፍ፣ በመስዋእትነቱ የደም ባህር ፈጥሮ መጭውን ትውልድ ወደነፃነት ማሻገርን መርጧል፡፡ ለዚህም ነው ጎንደር፣ ወሎ፣ ሸዋና ጎጃም የዐማራ አንገቱ አንድ ነው ብሎ በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ መንጋ ላይ የተነሳበት፡፡፡ በዚህ ሳያበቃ የወያኔን የክፋትና የወንጀል ጥግ የተረዱ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ወያኔና የጥፋት አጋሮቹን ለማጥፋት በሰንደቅ ዓላማው ምለው ተነስተዋል፡፡
ወያኔ ትላንት ከወራሪው ዚያድባሬ ጎን ወግኖ ኢትዮጵያን እንደወጋው ኹሉ ዛሬም ይህንኑ የክህደትና የባንዳነት ታሪኩን በመድገም ላይ ነው፡፡ ይህም ኾኖ በኢትዮጵያ ልጆች የተባበረ ክንድ ወደተመኘው ሲዖል ይላካል፡፡ የግፉዓን ኢትዮጵያውያን እንባም በአጠረ ግዜ እንደሚታበስ እምነት አለን፡፡ ለዚህ የሚከፈለውን ትርጉም ያለው መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን!!
ደማችን እንደተከዜ ወንዝ ይፈሳል እንጂ የሰማዕታት አደራ አይታጠፍም!
በዐማራ ክልላዊ መንግሥት
የወልቃይት፣ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳደር
ጥቅምት 30-2014 ዓ.ም.
ማይካድራ ከተማ