❝ኢትዮጵያውያን ፍላጎታቸውን ሊጭኑባቸው ለሚፈልጉ የውስጥና የውጪ ሃይሎች እጅ መስጠት የለባቸውም❞ ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ

837

❝ኢትዮጵያውያን ፍላጎታቸውን ሊጭኑባቸው ለሚፈልጉ የውስጥና የውጪ ሃይሎች እጅ መስጠት የለባቸውም❞ ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ

ጥቅምት 28/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ❝ኢትዮጵያውያን ፍላጎታቸውን ሊጭኑባቸው ለሚፈልጉ የውስጥና የውጪ ሃይሎች እጅ መስጠት የለባቸውም❞ስትል ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ ገለጸች።

ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ በትዊተር ገጿ ላይ ባሰፈረችው መልዕክት ሰብዓዊነትን በማጥፋት የራሳቸውን ከልክ ያለፈ ስግብግብነትና ሀብት ማስጠበቅ ፍላጎታቸው ለሆኑ የውስጥና የውጪ ኃይሎች ኢትዮጵያውያን እጅ መስጠት የለባቸውም ብለለች።

ዛሬ በአዲስ አበባ በተካሄደው ሰልፍ ላይ የተገኙት ዜጎች በተቀናጀ መልኩ ጥቃት እየተሰነዘረበት ያለውን መሰረታዊ መብታቸውን ለማስከበርና ለመጠበቅ እንደተካሄደ መግለጿን ኢዜአ ዘግቧል።

“ስግብግቦችና ተንኮለኞች የዋህነትን እንደ ድክመት እያዩ ሁልጊዜ ይሳሳታሉ” ብላለች።

Previous article❝የገጠመንን የህልውና አደጋ በመገንዘብ ሁሉም ሕዝብ ለህልውና ዘመቻው የራሱን አስተዋጽኦ ማድረግ ይገባዋል❞ አቶ የሱፍ ኢብራሂም
Next article“ለድል በሚገሰግስ መንፈስ የኢትዮጵያን አሸናፊነት እናበስራለን” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ