በውጭ ሀገራት የሚኖሩ የጂንካ ተወላጆች እና የአማራ ወዳጆች ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ፡፡

180

በውጭ ሀገራት የሚኖሩ የጂንካ ተወላጆች እና የአማራ ወዳጆች ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ፡፡

ደብረብርሃን: ጥቅምት 28/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በውጭ ሀገራት የሚኖሩ የጂንካ ተወላጆች እና የአማራ ወዳጆች በሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይል ወረራ ከወሎ የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን ከተማ ለተጠለሉ ወገኖች 760 ሺህ ብር ግምት ያለው ምግብና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።

የሸዋ ቀጣና የህልውና ዘመቻው አስተባባሪ ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው በተለይ ወጣቱ ተፈናቅሎ ተረጂ ከመሆን ይልቅ የህልውና ዘመቻውን መቀላቀል እንዳለበት ተናግረዋል።

ተፈናቃዮቹ ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

ለመዝመትና ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይልን ለመዋጋት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ዘጋቢ፡- ለዓለም ለይኩን -ከደብረብርሃን

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article“በኢትዮጵያዊነት ዝናብ የፈሰሰው ማዕበል ማጥለቅለቅ ጀምሯል”
Next articleበአማራ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ እንደሚሠራ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ድጋፍ አስተባባሪ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ዶክተር ካትሪን ሱዚ ገለጹ።