“ሴቶች እየተደፈሩ እና እናት አባቶቻችን እየተገደሉ ማንንም ቆሜ ላስተምር አልችልም” መምህርት ምዕራፍ ፍቃዴ

149
ደብረ ታቦር፡ ጥቅምት 26/2014 ዓ.ም (አሚኮ) መምህርት ምዕራፍ ፍቃዴ በጉና በጌምድር ወረዳ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምሕርት ናት፡፡ አሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ኀይል በኅብረተሰቡ ላይ እያደረሰ ያለውን ሰቆቃ ቁጭ ብላ ማየትና መስማት ሕሊናዋ አልፈቀደም፡፡ እናም ይህን ኀይል ያለበት ድረስ ሄዳ ለመፋለም ከደቡብ ጎንደር ዞን ታጣቂዎች ጋር ወደ ግንባር ዘመተች እንጂ፡፡ መምሕርት ምዕራፍ እንደሌሎች አካባቢዎች ወራሪው ቡድን በአካባቢዋ እስኪደርስ መጠበቅ እንደማያስፈልግ ተናግራለች፡፡
“ሴቶች እየተደፈሩ እናት አባቶቻችን እየተገደሉ ማንንም ቆሜ ላስተምር አልችልም” ያለችው መምህርት ምዕራፍ ቤት ድረስ መጥተው እስከሚደፍሩ እና እስከሚገድሉ ድረስ ከመጠበቅ ይልቅ ግንባር ላይ የጀግና ሞት መሞት እንደሚገባ ለአሚኮ ተናግራለች፡፡ መምህርቷ ሀገር ሰላም ሳትሆን በነጻነት መንቀሳቀስ፣ ሠርቶ መብላትም ሆነ ደመወዝ ማግኘት እንደማይቻልም ነው ያስረዳችው፡፡
“ሀገር ተደፍሮ እየተሸማቀቅን መኖር ስለሌለብን እስከመጨረሻው ድረስ ተፋልሜ ጠላት ሳይቀበር ወደ ቤቴ አልመለስም” ብላናለች መምህርት ምዕራፍ፡፡ ለሕልውና ዘመቻው የድርሻዋን ለመወጣት በምትችለው ሁሉ ጠላትን ለመፋለም ከዘማች ወንድሞቿ ጋር ዘምታለች፡፡ “ከሀገር በፊት የሚቀድም ምንም ነገር የለም” ያለችው መምህርቷ ጠላት ላይመለስ ተቀብሮ የአማራ ሕዝብ ነጻ ሲወጣ ያን ጊዜ አስተምራለሁ በማለትም ለትግሉ ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጣለች፡፡
ዘጋቢ፡- ደጀኔ በቀለ-ከጉና በጌምድር
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበሕልውና ዘመቻው ያልተሳተፈውን ከወራሪው ለይተን አናየውም❞ የቦረና ወረዳና የመካነ ሰላም ከተማ ነዋሪዎች
Next article❝ራሳችንን ነፃ ለማውጣት፣ ክብራችንና ታሪካችንን ለመጠበቅ የምንሰስተው ሕይወት አይኖርም❞ የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አብዱ ሁሴን