ለቀድሞ የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት ጥሪ ቀረበ።

83
ጥቅምት 26/2014 (አሚኮ) የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ለቀድሞ የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት ጥሪ አቀረበ፡፡
የጥሪ ማስታወቂያው ሙሉ ዝርዝር ቀጥሎ ቀርቧል፡-
ሀገርን የማፍረስ ሴራን በማክሸፍ ሀገርን የማዳን ዘመቻ ላይ ባላቸው እውቀት ልምድ እና አቅም ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጎን በመሰለፍ ይህ አፍራሽ ኃይል እስኪደመሰስ ድረስ የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት ባላቸው ተነሳሽነት ከሀገር መከላከያ ጎን በመቆም አቅማቸውና እውቀታቸው የፈቀደውን አስተዋጽኦ ለማበርከት ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
በዚሁ መሠረት ይህንን ተልዕኮ መወጣት የሚያስችል አካላዊ ሁኔታ ፣ የጤና ፣ የሥነ-አዕምሮ ዝግጁነት ፣ እውቀት እና ልምድ ያላቸውን አባላት ከዚህ በታች የተቀመጠውን መስፈርት ለሚያሟሉ የቀድሞ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት የወጣ መስፈርት፡፡
1. አጠቃላይ መስፈርቶች
1.1. የኢፊዴሪ ሕገ – መንግሥትን የተቀበሉ ፣
1.2. በሕዝቦች ሉዓላዊነትና አንድነት የሚያምኑ እና በፅናት ለማገልገል ሙሉ ፍቃደኝነት ያላቸው፣
1.3. ከማንኛውም የፖለቲካ ድርጅቶች ወገናዊነት ነፃ የሆኑ፣
1.4. በወንጀል ይሁን በፍታብሄር ተከሶ የፍርድ ቤት ክርክር የሌለባቸው፣
1.5. መከላከያ የሚያሰማራቸው የጦር ክፍሎች ሁሉ ተዘዋውረው ለመሥራት ሙሉ ፍቃደኛ የሆኑና የአካል ብቃት ያላቸው ፣
1.6. ለእግረኛ አዋጊ መኮንኖች ፣ ሻለቃ አመራርና ከዚያ በላይ ኃላፊነት የነበራቸው፣
1.7. በየትኛውም የማዕረግ ደረጃ ላይ በየማሰልጠኛ ማዕከላት አሰልጣኝ የነበሩ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣
1.8. የሜካናይዝድ እና የቡድን መሳሪያ አመራርና ምድብተኛ የነበሩ፣
1.9. የጤንነት ሁኔታን በተመለከተ
.የዓይን ፣ የአፍንጫ ፣ የጆሮ ፣ የጥርስ ፣ የከንፈር ችግር የሌለባቸው ፣
.ከቲቢ ፣ ከሚጥል በሽታ ፣ ከስኳር ፣ ከደም ግፊት ፣ ከኪንታሮት ፣ ከእንቅርት በሽታዎች ነፃ የሆኑ እና ለእንቅስቃሴ አስቸጋሪ የሆነ አካላዊ ችግር የሌለባቸው፣
1.10. የትምህርት ሁኔታ ማቀድ ፣ ማሠልጠን ፣ የስልጠና ዶክሜንት ማዘጋጀት የሚያስችል የትምህርት ዝግጅት ያለው ፣
1.11. በሚመለመልበት አካባቢ ከቀበሌ ፣ ከመሥተዳድር እና ከፖሊስ ከወንጀል ነፃ ስለመሆናቸው የጹሑፍ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣
1.12. የቀድሞ ጦር ሠራዊት አባል ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
2. ዕድሜን በተመለከተ፡-
2.1. ከወታደር እስከ ከፍተኛ የበታች ሹም ያሉ ከ55 ዓመት ያልበለጡ ፣
2.2. መስመራዊ መኮንኖች ከ60 ዓመት ያልበለጡ ፣
2.3. ከሻለቃ በላይ ያሉ ከፍተኛ መኮንኖች ከ64 ዓመት ያልበለጡ መሆን አለባቸው፡፡
3. የምልመላ ቦታና ጊዜ ፡-
. ለአዲስ አበባ ተመዝጋቢዎች በየክፍለ ከተማቸው ሲሆን
.ለክልል ተመዝጋቢዎች በየአካባቢያችሁ ባሉ የቀበሌ ፣ የወረዳ አስተዳደርና የጸጥታ ወይም ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት በአካል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን፣
. የምዝገባ ጊዜው ከኅዳር 01/2014 ዓ.ም እስከ ኅዳር 15 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ይሆናል፡፡
. በሁሉም የምዝገባ ጣቢያዎች ዝርዝር መስፈርቶች ተለጥፎ የሚገኙ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር
ጥቅምት 2014 ዓ/ም
አዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“ሁሉም ጨርቄን ማቄን ሳይል መዝመት አለበት”
Next article“አሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ኀይልን በከፍተኛ ሕዝባዊ ማዕበል እየደመሰስነው ነው” የአበርገሌ ወረዳ ነዋሪዎች