
ባሕር ዳር፡ መስከረም 20/2012 ዓ/ም (አብመድ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶክተር) የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ልዩ ልዑክን ተቀብለው አነጋገሩ፡፡ ልዑኩ ከፕሬዝዳንት የተላከ መልዕክትንም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅርቧል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በሁለትዮሽና ቀጠናዊ ግንኙነቶች ዙሪያ ከልዑኩ ጋር ሊመክሩ እንደሚችሉም የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡