
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 25/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው ትህነግ ሀገር የማፍረስ እቅድ ነድፎ መንቀሳቀስ ከጀመረ ድፍን አንድ ዓመት ተቆጥሯል። ቡድኑ በጥቅምት ወር 2013 ዓ.ም በሰሜን እዝ ላይ ያሰበው እቅድ እንዳሰበው አልሆን ሲለው የትግራይን ህዝብ በሀሰት ፕሮፓጋንዳ በማሰባሰብ ለዳግም የክህደት ተግባር በተለያዩ ግንባሮች ጦርነት ከፍቶ ይገኛል።
የሽብር ቡድኑ ሰሞኑን እጅግ በርካታ ቁጥር ያለው የሰው ኀይል በማሰለፍ በደሴ ግንባር ውግያ ቢከፍትም በርካታ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ሊደርስበት ችሏል።
በዚህ ግንባር ሰራዊቱ ባደረገው ዘመቻም በርካታ የጠላት ሃይልን የደመሰሰ ሲሆን በርካቶችንም ማርኳል። ከተማረኩት ውስጥም የሜይዴይ ክፍለ ጦር አዛዥ የሆነው የ64 አመቱ ኮ/ል ጉዕሽ ገብሩ ይገኝበታል።
እንደ ምርኮኛው ገለፃ የሽብር ቡድኑ ያሰማራው ሃይል ዲስፒሊን የሌለው በመሆኑ በወረራቸው አካባቢዎች በርካታ የግድያና ዘረፋ ተግባራትን አከናውኗል ።
የሽብር ቡድኑ ያሰባሰበው የሰው ሃይል ብዛት ከታጠቀው የመሳሪያ ብዛት ጋር የሚመጣጠን ባለመሆኑ አብዛኛውን የሰው ሃይሉን በባዶ ዕጅ በማሰለፍ የጥይት ሲሳይ እያደረገው እንደሚገኝም ተናግሯል ።
በአሁኑ ሰዓት በሽብር ቡድኑ አመራሮች እብደትና ቅሌት ምክንያት የትግራይ ህዝብ በከፍተኛ የሰላም እጦትና ችግር ውስጥ እንደሚገኝ የገለፀው ምርኮኛው ፣ የብሽር ቡድኑ አመራሮችን በቁጥጥር ስር ማዋል ብቸኛው መፍትሄ እንደሆነም ተናግሯል ።
መረጃው የመከላከያ ሠራዊት ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ