የአሸባሪው ትህነግ እኩይ ተግባሪዎች አጠገባችን አሉ፤ ሁላችንም እናጋልጥǃ

262

ጥቅምት 25/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሁን በየከተሞች የፌደራል ፖሊስ ፣ የመከላከያ ሠራዊት እና የተለያዩ የፀጥታ ኃይሎች አልባሳትን ለአሸባሪዎቹ ትህነግ እና ሸኔ ደጋፊ ኃይላት ሰፍተው በማዘጋጀት ላይ ያሉ ታድነው እየታዙ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡
በሰሜን ወሎ እና ተያያዥ ቦታዎች እንደታየው እና በቀጣይ ሌሎች ከተሞችም በተስተዋለው መሰረት የጥፋት ኃይላትን በከተሞች ታዩ ብሎ በፎቶ ለማሳየት የሚደረገው ቅንጅታዊ እንቅስቃሴዎችን የሀገር ደኅንነት ኃይላት አንጥረው እያጋለጡ ይገኛሉ።
ከእነዚህ የተቀናጀ የአሸባሪ ቡድን እንቅስቃሴ ውስጥ በየከተሞች የመከላከያ እና ሌሎች ፀጥታ ኃይላትን ዩኒፎርሞች አሰፍቶ በምልምል የአሸባሪ አድብቶ ጠባቂ ኃይል በማስለበስ ከተሞች ተያዙ የሚል የሽብር ተግባሮች እየተከናወነ ይገኛል።
የሀገር መከላከያ ዩኒፎርሞችን በመልበስ ሕዝብን በቀጥታ በመግደል ፤ “በስመ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሕዝብን እየጨረሰ ይገኛል” የሚል ክስ መንግሥት ላይ ለማቅረብም ጥረት እያደረጉ እንደሆነም ቅድመ መረጃዎች እየተገኙ ነው።
ሕዝብ ለሕዝብ የማጫረስ ተግባርን ልክ እንደ ገድል እና ጥበብ የሚቆጥረው የጁንታው ርዝራዥ እና ተላላኪው ሸኔ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ የሚቀበርበትን ወቅት እንደ ጣረሞት የሚቆጥረው እንደሆነ ተረጋግጧል። ይህንን የጸጥታ ኃይላትን ልብስ እየሰፋ ያለውን እና ለጥቃቅን ጥቅም ሲል የጥፋት ኃይልን የማገዝ ፍላጎት የሚያሳይ ማንኛውንም ኃይልን ከመካከላችን የማጋለጥ ሥራ ሁላችንም ልንሠራ ይገባል ተብሏል።
ክተት፣ ዝመት፣ መክት፣ አንክት!

Previous articleየአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ መዋቅር እና አደረጃጀት መመሪያ
Next articleየአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሽብርተኞችን እና የተላላኪዎቻቸውን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር እና አፋጣኝ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚያግዝ የሕግ ባለሙያ ገለጹ፡