
ባሕር ዳር፡ መስከረም 20/2012 ዓ/ም (አብመድ) የአማራ መልሶ መቋቋምና ልማት ድርጅት (አመልድ) በባሕር ዳር ከተማ ከፍተኛ ጥራት ያለውና በርካታ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ጋራዥ ለማቋቋም እየሠራ ነው፡፡
የአመልድ ዋና ዳይሬክተር ዓለማየሁ ዋሴ (ዶክተር) እንደተናገሩት ድርጅቱ በ20 ሚሊዮን ብር ነው ጋራዡን በባሕር ዳር የሚገነባው፡፡ ጋራዡ ለድርጅቱ የገቢ ማስገኛ ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን የሚገኘው ትርፍም በክልሉ ለሚሠሩ የልማት ሥራዎች ማጠናከሪያ እንደሚውልም ተመላክቷል፡፡
ዳይሬክተሩ እንዳሉትም ጋራዡ የአመልድ፣ የመንግሥት፣ የድርጅቶችና የግል ተሽከርካሪዎችን የመመርመርና የመጠገን አገልግሎት ለመስጠት የሚችል ነው፡፡
ጋራዡ በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ውስጥ ወደ ሥራ ለማስገባት አመልድ ጥረት እያደረገ እንደሆነም ተገልጿል፡፡
ምንጭ፡- አመልድ