
ጥቅምት 25/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ አየር ኃይል ከመቼው ጊዜ በላይ አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ኃይል ድባቅ ለመምታትና ግብዓተ መሬቱን ለመፈፀም የሚያስችል ሥራ በብቃት እያከናወነ መሆኑን አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ምክትል አዛዥና የሎጅስቲክ አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ነገራ ሌሊሳ እንደገለጹት፤ አየር ኃይሉ ከመቼው ጊዜ በላይ አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ኃይል ድባቅ ለመምታትና ግብዓተ መሬቱን ለመፈፀም የሚያስችል ሥራ እየሠራ ነው።
ተቋሙን በቴክኖሎጂም ሆነ በሰው ኃይል አደረጃጀት አቅሙን ለማሳደግ ከሚደረገው ሁለንተናዊ ጥረት ጎን ለጎን በሀገር ላይ የተቃጣውን ወረራ ለማክሸፍም አኩሪ ተግባርና ታላቅ ጀብዱ እየፈፀመ መሆኑን አስረድተዋል።
አየር ኃይሉ አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ኃይል ሞት እንዲፋጠን የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ እየተወጣ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የአሸባሪ ኃይሉን እንቅስቃሴ እየተከታተለ ድባቅ እየመታው እንደሚገኘም መግለጻቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ