ምክር ቤቱ የቀረበለትን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አጸደቀ፡፡

186
አዲስ አበባ፡ ጥቅምት 25/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለስድስት ወራት ተፈጻሚ የሚሆን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርምሮ አጸደቀ።
ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 1ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ስብሰባው ከሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበለትን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርምሮ አጽድቋል።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጥቅምት 23/2014 ዓ.ም ባካሔደው 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባው በሀገር ህልውና ሉዓላዊነት ላይ የተደቀነውን አደጋ ለመከላከል ያወጣውን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 5/14 ለማጽደቅ የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ አጽድቋል።
ምክር ቤቱ በተጨማሪም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አባላት ለመሰየም የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ ለማጽደቅ እየተወያየ ነው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleእብናት ልጆቿን ወደ ግንባር ሸኘች፡፡
Next articleአየር ኃይሉ አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ኃይል ድባቅ እየመታ ነው፡፡