❝የወገንን ህልፈት እና መፈናቀል ለማስቆም ወጣቶች ወደ ግንባር መዝመት ይገባቸዋል❞ ኮሚሽነር ዘላለም ልጃለም

203
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል አደጋ መከላከል፣ ምግብ ዋስትና ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘላለም ልጃለም አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል ወረራ ያደረሰውን ማኅበራዊ ቀውስ እና መደረግ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
አቶ ዘላለም እንዳሉት በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኀይል በሰሜን እና ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ እና ዋግ አካባቢዎች ከ994 ሺህ በላይ የኅብረተሰብ ክፍል ተፈናቅሏል፡፡ አሸባሪው ቡድን በወረራቸው አካባቢዎችም 5 ሚሊዮን ሕዝብ በችግር ውስጥ መኾኑን ነው ያብራሩት፡፡
በሽብር ቡድኑ በተያዙት አካባቢዎች በንጹሐን ላይ ከሚፈጽመው ግድያ በተጨማሪ እናቶች፣ ሕጻናት እና ተመላላሽ ታካሚዎች በምግብ፣ በውኃ እና በመድኃኒት እጦት ምክንያት ሕይወታቸው ማለፉን ገልጸዋል፡፡ በዚህም በሰሜን ወሎ መቄት አካባቢ ከ90 በላይ ሰዎች በሕክምና እጦት፣ 13 እናቶች በወሊድ ችግር፣ በዋግኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ጋዝጊብላ እና ዝቋላ ደግሞ 13 ሰዎች በምግብ እና በመድኃኒት እጦት ምክንያት ሕይወታቸው ማለፉን ለአብነት አንስተዋል፡፡
የሕዝቡ ስቃይ እና ችግርም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡
ዓለም አቀፍ ረጂ ድርጅቶች ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቢደረግም ለመደገፍ ፍላጎት አለማሳየታቸውን አንስተዋል፡፡ ችግሩን ለመሻገር ማኅበረሰቡ፣ መንግሥት እና ውስን መንግሥታዊ ያልኾኑ ድርጅቶች ድጋፍ ማድረጋቸውን ጠቁመዋል፡፡
ለተፈናቀሉ ወገኖች ማኅበረሰቡ እያደረገ ያለው የቆየ የመደጋገፍ ባሕል መልካም ቢኾንም የማኅበረሰቡን መፈናቀል እና ህልፈት ማስቆም እና ዘላቂ ማኅበራዊ ረፍት ማምጣት የሚቻለው ወጣቱ መንግሥት ያስተላለፈውን የክተት ጥሪ ተቀብሎ በመዝመት የሽብር ቡድኑን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ መደምሰስ ሲቻል መኾኑን አስገንዝበዋል፡፡ ወጣቱ ታሪካዊ ግዴታውን እንዲወጣም ኮሚሽነሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ዳግማዊ ተሠራ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article❝ከአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል የተቃጣብንን የሕልውና ሥጋት ለመቀልበስ ጽናት እና ቁርጠኝነት የትግሉ መርህ ሊሆን ይገባል❞ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ
Next articleእብናት ልጆቿን ወደ ግንባር ሸኘች፡፡