የአፋር ክልል ነዋሪ ያለውን ማንኛውንም የነፍስ ወከፍ መሣሪያ በመያዝ እንዲዘምት ጥሪ ቀረበ።

167
ጥቅምት 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአፋር ክልል ነዋሪ ያለውን ማናቸውንም የነፍስ ወከፍ መሣሪያና ትጥቅ እንዲሁም ተያያዥ ግብዓቶች በመጠቀም ከልዩ ኃይሉና መከላከያ ሠራዊቱ ጎን በመሠለፍ ሕዝቡ ከተደቀነበት አደጋ እንዲታደግ ክልሉ ጥሪ አቅርቧል።
የአፋር ክልል ርእሰ መሥተዳድር አወል አርባ ወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ እንዳሳሰቡት፤ የክልሉ ሕዝብ ኢትዮጵያን ለመከፋፈልና ለመበተን የሚንቀሳቀሰውን ወራሪ ኃይል መግታት ይጠበቅበታል።
አሸባሪ ኃይሉ በክልሉ የተለያዩ ወረዳዎች ለመግባት ቢሞክርም አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ በወረራ ከያዛቸዉ አካባቢዎች መባረሩን ገልጸዋል።
ቡድኑ በወረራ ይዟቸዉ በነበሩ አካባቢዎች ሴቶችና ሕፃናትን ጨምሮ ንፁሐንን በግፍ መጨፍጨፉን እና መሠረተ ልማቶች በማውደም አስታውሰዋል።
ይህንን የቡድኑን ጸያፍና ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ታሪክ በነውርነቱ የሚያስታውሰው ጥቁር ጠባሳ መሆኑን መግለጻቸውን ኢብኮ ዘግቧል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleነገ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የተዘጋጀ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ እንደሚጸድቅ ተገለጸ።
Next article‹‹የማይካድራው ጭፍጨፋ በሕወሓት መዋቅር ተፈፅሟል›› ሪፖርት