
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በሃገር ህልውናና ሉአላዊነት ላይ የተደቀነውን አደጋ ለመከላከል በሚኒስትሮች ምክር ቤት የተዘጋጀ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ነገ ለም/ቤቱ ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኃላ ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በኢፌደሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 93/1 የውጪ ወረራ ሲያጋጥም ወይም ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ሲከሰትና በተለመደው የህግ ማስከበር ስርዓት ለመቋቁም የማይቻል ሲሆን፣ ማንኛውም የተፈጥሮ አደጋ ሲያጋጥም ወይም የህዝብን ጤንነት አደጋ ላይ የሚጥል በሽታ ሲከሰት፣ የፌዴራሉ መንግስት የሚኒስትሮች ም/ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የማውጣት ሥልጣን እንዳለው ይደነግጋል፡፡
በዚሁ አንቀጽ 2(ሀ) የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በሥራ ላይ ባለ ጊዜ የታወጀ ከሆነ በታወጀ በ48 ሰዓታት ውስጥ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መቅረብ አለበት በሚል ተደንግጓል ፡፡
በመሆኑም በሚኒስትሮች ም/ቤት የተዘጋጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ነገ ለም/ቤቱ ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኃላ ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
መረጃው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ