
ባሕር ዳር፡ መስከረም 20/2012 ዓ/ም (አብመድ) 7ተኛው የኢትዮ-ሩስያ የጋራ ኮሚሽን ጉባኤ ኢኮኖሚያዊ፣ ሳይንሳዊ፣ ቴክኒካዊና የንግድ ትብብር አጀንዳዎች ላይ አተኩሮ በሩሲያ ፒተርስበርግ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
የኢፌዴሪ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ጌታሁን መኩሪያ (ዶክተር ኢንጂነር) የተመራ የልዑክ በጉባኤው ላይ እየተሳተፈ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
በጉባኤው የንግድ ትብብር፣ የኢኮኖሚ ትብብር፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የአማራጭ የኃይል ምንጮች፣ የህዋ ቴክኖሎጂ፣ የዲጅታል ቴክኖሎጅ መገናኛ ዘዴዎች፣ የባሕልና ቱሪዝምና ሌሎች አዳዲስ የትብብር ማዕቀፎችና የትኩረት ዘርፎች ላይ ያተኮሩ ዝርዝር ጉዳዮች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸውም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የኒውክለር ኃይል አማራጮችን ለሠላማዊ አገልግሎት በስፋት ለመጠቀም የሚያስችል ፕሮቶኮልም አንዱ የመወያያ አጀንዳ እንደሆነ ነው የተገለጸው፡፡
ከጉባኤው ኢትዮጵያ እያካሄደቻቸው ላሉ ሀገራዊ ለውጦች
አጋዥ የሆኑ የትብብር ማዕቀፎችና ስምምነቶች ግብዓት ያገኛሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡
ኢትዮጵያ እና ሩስያ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ ግንኙነት አላቸው፡፡