የአማራ ክልል መንግሥት ያስተላለፈውን የክተት ጥሪ የተቀበሉ የጎንደር ፋኖና ሚሊሻ አባላት ሽኝት ተደረገላቸው።

360
ጎንደር፡ ጥቅምት 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ኃይል በአማራ ብሎም በኢትዮጵያ ላይ የደቀነውን አደጋ ለመቀልበስ የክተት ጥሪ ተላልፏል። የክልሉን መንግሥት ጥሪ የተቀበሉ የጎንደር ፋኖና የሚሊሻ አባላት የሽብር ቡድኑን ለመፋለም ሽኝት ተደርጎላቸዋል።
በአሸኛኘት ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ዘማቾቹን አበረታተዋል። አማራን ከታሪክ ውርደት ለማዳንና ኢትዮጵያን ለማስቀጠል የሚደረገውን መስዋእትነት ታሪክ ሲዘክረው ይኖራልም ብለዋል አቶ መላኩ አለበል።
እየተደረገ ያለው ዘመቻ ለነጻነትና ለፍትሕ ነውና ሁሉም ሊዘምትና ሊታገል ይገባል ነው ያሉት። የአባቶቻችንን ታሪክ ከማውራትም ባለፈ የራሳችንን ታሪክ መሥራት እንደሚገባም አቶ መላኩ ገልጸዋል።
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዘውዱ ማለደ የሽብር ቡድኑን ለመፋለም ከሚዘምቱ ዘማቾች በተጨማሪ ጎንደርና አካባቢውን ለመጠበቅ ሁላችንም ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባልም ብለዋል።
የክተት ጥሪውን ተቀብለው የተሰባሰቡት የፋኖና የሚሊሻ አባላት በበኩላቸው አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ኃይል ለመደምሰስ ቆርጠው መነሳታቸውን ገልጸዋል።
በከተማና በተለያዩ አካባቢዎች ያልዘመተው የኅብረተሰብ ክፍል አካባቢውን ከሰርጎ ገቦች በመጠበቅ የሽብር ቡድኑን መቃብር ማፋጠን እንደሚገባም ዘማቾቹ ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡- ደስታ ካሳ – ከጎንደር
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleባንዳዎችን ከኢትዮጵያ ታሪክ የመሰረዝ ወቅቱ አሁን ነው!
Next articleሕዝባዊ ማዕበል አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ኃይል ለመደምሰስ…