“ነፃነትና ክብርን በችሮታ ማግኘት አይቻልም!” የገቢዎች ሚኒስትር ላቀ አያሌው

285
ጥቅምት 22/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የገቢዎች ሚኒስትር ላቀ አያሌው በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት “ነፃነትና ክብርን በችሮታ ማግኘት አይቻልም!” ብለዋል፡፡
የትግራይ ወራሪ ኃይል እየፈጸመ ያለውን ወረራና ግፍ ማስቆምና የድል ባለቤት መሆን የሚቻለው በጋራ ሕልውና ላይ የተቃጣውን አደጋ በጋራ ሆኖ በመቆምና ወደ ተግባር በመቀየር ብቻ ነው፤ ነፃነትና ክብር የሚገኘውም በዚህ ተግባራዊ ሥራ ብቻ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ድል የሚመዘገበው በእያንዳንዱ በሚያዝና በሚለቀቅ ቦታ ሳይሆን በጦርነቱ አጠቃላይ ፍፃሜ ላይ የአሸናፊነቱን ዋንጫ በመውሰድ ነው ያሉት አቶ ላቀ በቁጭት እልህና ወኔ እንዲሁም ከመቼውም ጊዜ በላይ ሁሉም የአማራ ሕዝብ ሌሎች አጀንዳዎች እንኳን ቢኖሩት ከድል በኋላ ይደርሳል በሚል እሳቤ አንድ ሆነን በጠላት ላይ የጋራ ክንዳችንን ማሳረፍ ይኖርብናል ብለዋል፡፡
የክልሉ መንግሥት ያስተላለፈውን ጥሪ ተቀብሎ ሁሉም በግንባር ላይ በመገኘት የድርሻውን መወጣት ግድ የሚልበት ወቅት መሆኑን አመላክተዋል፡፡
“እስካሁን በአያትና ቅድመ አያቶቻችን ድል ቆይተናል። ነገር ግን ዛሬ ተራው የእኛ ስለሆነ የተበላሸ ታሪክ የሌለውን ሕዝብና ሀገር በእኛ ዘመን በፍፁም የተሻለ እንጅ ያነሰ ልንሠራ አይገባም፤ ነፃነትና ክብር በችሮታ ስለማይገኝ በራሳችን መስዋእትነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት መሥራት ይጠበቅብናል” ነው ያሉት፡፡
በማወቅም ኾነ ባለማወቅ የጠላትን አሉቧልታ ለሌላ አካል ከማስተላለፍ መቆጠብ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“ወደ ግንባር ለመዝመት ተዘጋጅተናል” በደባርቅ ከተማ የተጠለሉ ተፈናቃዮች
Next articleባንዳዎችን ከኢትዮጵያ ታሪክ የመሰረዝ ወቅቱ አሁን ነው!